ወያኔና ISIS – የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች!

ከቴዎድሮስ ሓይሌ

TPLF = ISISሰሞኑን በየመን በደቡብ አፍሪካ በወገኖቻችን ላይ የደረሰው የሞት አደጋ የፈጠረው ህዝባዊ ቁጭትና ሃዘን ሳይበርድ ይባስ ብሎ በሊብያ በዚህ ዘመን ይፈጸማል ብሎ ለማሰብ የሚከብድ አረመኔያዊ በሆነ መልኩ በግፍ የተሰየፉትን ወንድሞቻችን የተቀላ አንገት ተመልክተናል ። ይህ የሽብር ድርጊት ለእኛ ለባለቤቶቹ እይደለም መላው አለምን ያስደነገጠና ያሳዘነ አጋጣሚ ነው። እንድ ዜጋ የተዋረድንብት ግዜ ቢኖር አሁን ነው! ትውልዱ ሃገር ቤት ካለው የትግሬ ወያኔዎች ግፍ ግድያ እስርና ሞት ለማምለልጥ ፤ የዘረኛው ቡድን አድሏዊነት በፈጠረው የአንድ አናሳ ቡድን የኢኮኖሚ የበላይነት በሃገሩ ነግዶ ና ያገኘውን ሠርቶ እንዳይኖር የሚያድርግ ጭቆና የፈጠረውን የኑሮ ውድነትና ያስከተለውን ረሃብና እርዛት ለመሸሽ እግሩ ወደ መራው ስደት ይሄድ ዘንድ በመገደዱ በዓለም ውስጥ እንደ ጨው ዘር ተበትኖ ይህው ሰሞኑን እንዳየንና እንደሰማነው የመከራ ውርጅብኝ በዝቶበት የአንዱ ችግር ሳይቀረፍ ሌላው እየተተካ ለኢትዮጽያ ሕዝብ ምጽዕት የቀረበ እስኪመስል ድረስ ይህው በሃዘንና በትካዜ ላይ ወድቀን እንገኛለን።

ኢትዮጽያዊነት ክብርና ኩራት ጀግንነትና አትንኩኝ ባይነት እንግዳ ተቀባይነት ደግነት የመሆኑ ታሪክ ተለውጦ አዋርደው ለውርደት ገለው ለገዳይ ሰድበው ለሰዳቢ አሳልፈው የሰጡን የሃገራችን አንጡራ ሃብት እየዘረፉ በቅንጦት ህይወት አለማቸውን ከመቅጨት በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ከሃገር አሽሸተው ሰርቶ የመኖር ነግዶ የመክበር አርሶና ቆፍሮ ኑሮን የማሸነፉን እድል ያሰጡት ትውልድ ህይወት ቢከብደው ተስፋው ቢጨልም ስደትን አማራጭ አድርጎ በላብ በወዙ ጥሮ ግሮ ህይወቱን ሊለውጥ ቤተሰቡን ሊረዳ የሄደበት የመከራ መንገድ እሱም በዝቶ ይህው በሃገሩ መኖር አቅቶት የደረሰበት መንገላታት አንሶ እንደ ከብት በባርንት በዚህ ዘመን ከመሸጥ መለወጡም በላይ ይህው በሊብያ ኢንደታይው ለጅምላ እርድ ለመዳረግ በቅቷል። ይህ ሁሉ ሲሆን ትውልዱን በግፍ አስመርሮ ከሃገሩ እንዳላባረሩት የትግሬ ወያኔዎች ዓለማቀፍ ሚድያዎች እየተቀባበሉ የዘገቡትን ራሱ የሽብር ቡድን በለቀቀው የቪድዮ መልዕክት ላይ በግልጽ እየተናገረ ቤተሰቦቻችው ሃዘን በተቀመጡበት ሁኔታ ላይ የሟቾቹን ማንነት ስለማጣራት በወያኔ ሚድያ የቀረበው ዘገባ ይበልጥ የሕዝባችንን ልብ የሰብረ ከመሆኑም በላይ የወያኔው ቡድን ለህዝቡ ያለውን ንቅትና የምንቸገረኝነት ትዕቢቱን ያስመሰከረበት አጋጣሚም ሆኖ ታይቷል የሌባ የውሸታም፤ የሃገር ሻጮች፤ ጥርቅም የሆነው የትግሬ ወያኔዎች ቡድን ሕዝብ ቢያልቅ፤ ትውልድ ቢፈጅ ከስልጣኑ ውጭ ደንታ የሌለው አራዊት እጅ ሃገራችን ከወደቀች ጀምሮ በህዝባችን ላይ የደረሰው ስቃይ ተዘርዝሮ አያልቅም ። የስልጣን ወንበራቸውን ህዝብን በህዝብ ላይ በማነሳሳት፤ በአሰቦት በበደኖ ፤ በወተር ፤ በአርባጉጉ ፤ ትላንት በአይሲስ ከተፈጸምው ባልተናነሰ ሁኔታ የእርጉዝ ሆድ እየተቀደደ፤ የሰው ቆዳው በቁም የተገፈፈበት ጊዜ አንስቶ እስከ ጋንቤላውና ኦጋዴን ድረስ የተፈጸመውን የጅምላ ግድያና የዘር ማጥፋት ተግባር ተጠምዶ የህዝባችንን ደም ሲመጥ የቆየው የወያኔ አገዛዝ ጎን ለጎን አባላቱንና ደጋፊዎቹን በግልጽ ዘረፋና አድሏዊነት በሃብት እንዲንበሸብሹ በማድረግ በኢትዮጽያ ታሪክ ታይቶ በማይታውቅ ሁኔታ የተፈጠሩት ሃብታሞች የሚግነቡት ቪላና የሚኖሩት ኑሮ የአውሮፓና የእሜሪካ ከበርቴዎች ከሚኖሩት በላይ እንደሆነ የሚታይ ሃቅ ነው።

ከዘመኑ የወያኔ ጭፍሮች አንዱ የዛሬ ሃያ አመት ከጎፈሬው ተባይና ከእግሩ ንቃቃት ውጭ እውቅትም ሆን ንግድ ያልነበረው ተራ ግለሰብ ከህዝብ በተዘረፈ ሃብት የተገነባ እጅግ ቅንጡ ቪላ ነው። ከዚህ ዘርፋ በስትጀርባ ስንት ወንጀል ተፈጽሟል ? ስንቱ ከቤቱ ከስራውና ከሃገሩ ተፈናቅሎ ለመከራ ተዳረገ። ዛሬ በሃገራችን የሚታይው እጅግ የተራራቀው የኑሮ ልዩነት ለጥቂቶች ገነት ለብዙሃኑ ሲዖል የሆነው ያለው ዘረኛ አገዛዝ ባነብረው አድሎዓዊነት ነው። መንግስታዊ ሌቦች ከነዘር ሰንሰለታችው የፈጠሩት የኑሮ መዘበራርቅ ይህው የሰሞኑን አይነት በትውልዱ ላይ የዘነበው መከራ እንዲከሰት አድርጓል ቀድሞ በሃገራችን የነበሩት ሃብታሞች በአብዛኛው የነበራችው ሃብትና ምንጩ የሚታወቅ ነበር።

ጨካኝ የተባሉት የደርግ መሪዎችና በጊዜው ስልጣን ላይ የነበሩት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ አብዛኞቹ በመንግስት የኪራይ ቤት ይኖሩ የነብሩ እንደነበርና ለመታወቁ ወያኔዎች ራሳቸው ጭምር ያረጋገጡት ሃቅ ነው የዛሬዎቹ የትግሬ ወያኔ መራሹ ‘’ታሪኬ ባጭሩ የሚባሉት ወፍ ዘራሽ ታጋይ ከበርቴዎች ከሃያ እመታት በፊት ይህ ነው የሚባል ገንዘብም ሆነ እውቀት ያልነበራችው የአገዛዙ ሰዎች በተከፈተላቸው የበቀል አካሄድ ሁሉንም የጥቅምና የገቢ ምንጮች በሞኖፖል በመቆጣጠር ሌላው ዜጋ ተቀጥሮ መስራትና ነጻነት በማጣቱ ነጋዴው ንብረቱን ሸጦ ተማሪውም ተስፋ ቆርጦ ሃገሩን ለቆ እየተሰደደ ይህው ዛሬ ከምድር ጫፍ እስከ ጫፍ ግንባር ቀደም ስደተኛ ሆነን ይህው ለሚሠማውና ለሚታየው መከራ ተዳርገናል ።

የመከራው የስቃዩ ወጀብ አሁንም አላበቃም ዛሬም በሊብያ በየስፍራው ተደብቀው በጭንቅና ስጋት ላይ ይገኛሉ። ሌሎችም በአፍሪካ ፤ በመካከለኛው ምስራቅ ፤ ድምጻቸውን ማሰማት ያልቻሉ የሚፈልጋችው መንግስት አቤት የሚሉበት ስፍራ ያጡ በባርነት የተያዙ አያሌ ኢትዮዽያውያን በጭለማ ተውጠው ይገኛሉ። የዚህ መከራ ማብቂያው መቼ ነው? በሃገር ኖረንም እስር ጭቆና ስራ እጥንትና ችጋር እያንጠራወዘን ስንቸገር ፤ ተሰደንም ሞት ስቃይና ውርደት ሲፍራርቅብን ፤ ሃገራችንን ነጥቀው ሃብትና ንብረታችንን ሠርቀውና ስብዕናችንን ገፈው ለእንዲህ አይነት ብሄራዊ ውርድት የዳረገን ዘረኛውና ዘራፊው የውያኔ ቡድን በተባበር ክንዳችን እስካላስውገድንው ድርስ ይህን ሃገር አዋራጅና ትውልድ አውዳሚ ድርጊት ከቶም መግታት አይቻልም።

ስለሆነም አዲሱ ትውልድ ወጣቱ ሆይ ስደት ይብቃህ ለለውጥ ተነስ ወይ በተገቢው ለመኖር አለያም ለክብር ሞት ራስህን አዘጋጅ የአህዛብ መቀለጃ የደደቦች መጫዎቻ የመሆን ታሪክህን አድስ፤ ሃገርህ እንኳን ላንተ ለሌሎችም የሚተርፍ ወርቅ ተፈጥሮ አላት፤ ከበረታህ አንተ ሳትሆን እነሱ ወዳንተ ይመጣሉ። ትላንትም በአባቶችህ ዘመን ክፉ ቀን በክብር ያሳለፉት ባንተ ሃገር ነበር፤ እንዲህ ሊያወርዱህ እድል ያገኙት ሃገርህን የወረረው የትግሬ ነፃ አውጪ ሌባ ቀማኛና ሰዶማዊ አገዛዝ ታፍሮና ተከብሮ የኖረ ሃገራዊና ታሪካዊ ክብርህን በዓለም ፊት ያቀለለ በመሆኑ ክንድህን ማንሳት ያለብህ በዚህ ሃገር በቀል የአረቦች የጭን ገረድ በሆነ የወያኔ አገዛዝ ላይ ነው ። ስለዚህም በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ በሰላም ይሁን በአመጽ በጓንዴ ይሁን በጎራዴ በቀለም ይሁን በፍራፍሬ አብዮት ስደት በቃኝ ብለህ አገርህን ሳትለቅ ለውርደትና ለስቃይ አሳልፎ የሠጠህን መሪር ጠላትህ የሆነውን የወያኔ ቡድን አፈርድሜ ለማስጋጥ ተነስ፤ ታጠቅ፤ ዝመት፤ የውርደት ማርከሻ መድሃኒቱ እንደአባቶችህ እንቢኝ በማለት ባንዳና ቅጥረኛውን ማስወገድ ብቻ ነው።

ይህ ደግሞ ይቻላል! ተችሏልም!! የግድ መቻልም አለበት!!