የህወሃት በቀቀኖች ሚሚ ስብሃቱና ባለቤቷ ዘሪሁን ተሾመ በዲሲ – አርአያ ተስፋማሪያም

ከMimi Sebhatuአርአያ ተስፋማሪያም

ጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱና ባለቤቷ ዘሪሁን በዲሲ እንደሚገኙ ታውቋል። ባላፈው ቅዳሜ ከዲሲ ከሚተላለፈውና ንጉሴ በተባለ “ጋዜጠኛ” ከሚሰናዳው ራዲዮ ጋር ቃለምልልስ ያደረገው ዘሪሁን በዲሲ በሚገኙ የሃበሻ ሬስቶራንቶች ከባለቤቱ ጋር ሲዝናና ኢትዮጵያውያን እየሰደቡት፣ እያስፈራሩትና አንዳንዶች ደግሞ ስልክ እየደወሉ በሱማሊኛ ቋንቋ ተቃውሟቸውን ከመግለፅ ባሻገር “ኢህአዴግ አባረራችሁ እንዴ?” እያሉ በፌዝ የጠየቁት እንዳሉ ተናግሯል። መሳደብና ማስፈራራት በህግ እንደሚያስጠይቅና አግባብም እንዳልሆነ አያይዞ ተናግሯል። በእርግጥም ስድብ የሚደገፍ አይደለም። ነገር ግን «ዛሚ» የተባለውና በእሱና ሚሚ ስም የሚታወቀው ራዲዮ የሚለቀው የስድብ ውርጅብኝ አግባብ ነው?..በሚሚ ያልተሰደበ፣ ያልተዘለፈ፣ ያልተንቋሸሸ ግልሰብና የህብረተስብ ክፍል አለ ይሆን?…”በራስህ ሊደረግብህ የማትሻውን በሌሎች አታድርግ” የሚባለው ለዚህ ነው። በተለይ በአንዲት የተቃዋሚ አመራር አባል ላይ ሚሚና ዘሪሁን የፈፀሙት እጅግ አስነዋሪ የወሲብ ቅንብር ድርጊት (ቪዲዮ) የሚረሳ አይደለም።…በነገራችን ላይ ሁለቱ ባለሃብቶቹን ተከትለው ነው የመጡት። ቱጃሮቹ ተመልሰዋል። ከነሱ ስር አልጠፋ ያሉበት ምስጢሩ ምን ይሆን?….ዘሪሁን ዲሲ ለሚገኙ ወዳጆቹ – ገዢው ፓርቲ በአውስትራሊያ አምባሳደር አድርጐ ሊሾመው እንደሆነ መናገሩ ታውቋል። ሌላው የሚሚና ዘሪሁን አስገራሚ ድርጊት ሳይጠቀሳ አይታለፍም፤ ቀን ከአረንጓዴዋ ቅጠል ጋር በሰላም ካሳለፉ በኋላ ማታ ውስኪ ሲጐነጩ ድብድብ መከተሉ ነው። አንዳንዴ ጠርሙስ እስከመወራወር እንደሚደርሱ ለሁለቱ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ገነነ አሰፋ ማሸማገሉ እንደሰለቸው ጭምር የሚናገረው ነው።

5 Comments on “የህወሃት በቀቀኖች ሚሚ ስብሃቱና ባለቤቷ ዘሪሁን ተሾመ በዲሲ – አርአያ ተስፋማሪያም”

  1. really I always follow you. because each in formation has its own value for me. thank you for your. I LOVE YOU SO MUCH

  2. These Bandas are enemies of the Ethiopian People and if possible one ca
    n even challenge them in a legal way.

  3. As the fantastic amharic saying goes “Gem legem aberehe azegm.” (the hasband & wife). The sherlatan journalist, meme sebehat, has neither a moral nor a legal right to criticize the womean not alone to talk about her private sexual life. meme as
    her father safering from Ethio-phobia, she needs esp. both Psychological and psychiatrici reatment. Most imoprtantly she has to go to “Tebel” for fast remedy. ALAS!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*