የኢትዮጵያ ፋሽን አለምን ይቆጣጠር ይሆን? ሲል ሲኤንኤን በዘገባው ይጠይቃል

የሲኤንኤን ኢንሳይድ አፍሪካ ዝግጅት ዛሬ መዳረሻው ኢትዮጵያ ነበረች፡፡ ሀገሪቱ አለም አቀፍ ሱፐር ሞዴሎች አሏት ሲል ሚጀምረው ይህ የሲኤንኤን ኢንሳይድ አፍሪካ ዘገባ ሞዴሎችም ብቻ ሳይሆን አለምአቀፍ ዝና ያላቸው ዲዛይነሮችና ምእተ አመታትን ያስቆጠረ የጨርቃጨርቅና ስፌት ባህልም ባለቤት ናት ይላል፡፡

የአዲስ አበባ የፋሽን ሳምንትን ካዘጋጁት አንዷ ማህሌት ተክለማሪያም የኢትዮጵያ የፋሽን አልባሳት ዛሬ ዛሬ በአለም ገበያ ተፈላጊነታቸው እንደጨመረ ትናገራለች ፡፡

ከዚህ ቀደም በፋሽን ኢንዱስትሪው ዘርፍ ኢትዮጵያ አትታወቅም ነበር የምትለዋ ማህሌት አሁን ላይ የቱርክ የቻይናና የሌሎች ሀገራት የጫማና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች ወደሀገሪቱ በሰፊው መግባታቸውን በመጥቀስ በዚህ ረገድ ሀገሪቱ ትልቅ ለውጥ ማምጣቷን ነው ለዘገባው ምታስረዳው፡፡

እኛ ብዙ ከምንነግራችሁ ይህንኑ በቪዲዮ የተቀናበረ ዘገባ ሙሉውን ብንጋብዛችሁ ይሻላልና እነሆ ጀባ ብለናችኋል፡፡

Could Ethiopian fashion go global CNN Video

 

The post የኢትዮጵያ ፋሽን አለምን ይቆጣጠር ይሆን? ሲል ሲኤንኤን በዘገባው ይጠይቃል appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.