የግብፅ እና የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ተወዛገቡ Disagreement between Ethiopian and Egypt security officers in Addis Abeba

ሰንደቅ ጋዜጣ

የኢትዮጵያ እና የግብፅ የንግድ የንግድ ማህበረሰብ ልዑካን አባላት ስብሰባ ትላንት በሸራተን አዲስ ሆቴል ሲካሄድ  የሁለቱም ሃገራት የጸጥታ ሠራተኞች ጋዜጠኞችን በማስገባት ባለመስማማታቸው ተወዛገቡ፡፡ 
     በግምት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ገደማ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የግብጹ ፕሬዚደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በተገኙበት የሁለቱ ሀገራት የንግድ ማህበረሰብ አባላት ባሰተፈው ስብሰባ ላይ ለመዘገብ የሄዱ የኢትዮጽያ ጋዜጠኞች በግብጽ የጸጥታ ኃይሎች ገብተው እንዳይዘግቡ የተከለከሉ ሲሆን የኢትዮጽያ የጸጥታ ኃይሎች በተቃራኒው ጋዜጠኞቹ ገብተው እንዲዘግቡ በመወሰናቸው ለጥቂት ደቂቃዎች አለመግባባትና ግርግር ተፈጥሯል፡፡  
ሆኖም ጋዜጠኞቹ እንዲገቡ በመፈቀዱ አለመግባባቱ ረግቧል፡፡
     በዚህ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ እና ግብፅ የንግድ ግንኙነት በየዓመቱ ለውጥ እያመጣ ቢሆንም አመታዊ የንግድ ልውውጡ መድረስ ይገባል ተብሎ ከተገመተው የአምስት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አንፃር ሲታይ ግን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገምግሟል።
     በኢትዮጵያ ለሚሰማሩ የግብፅ ባለሃብቶች ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያገኙ ነው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በውይይቱ ላይ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡
     በውይይቱ ላይ የግብፅ ፕሬዝዳን አብዱልፋታህ አል ሲሲ ሃገራቱ በዲፕሎማሲ መስክ እያሳዩት ያለውን ግንኙነት በኢኮኖሚ መስክም እንዲጠናከር ግብፅ ፍላጎቷ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

O0ezXZDQhCq3b8Wr290ISIuvwmlj7CK7ztvPloGB59DOxE51QPWsmiNd/soderemovies.png?width=256″ width=”256″ class=”align-left” /”>Watch Ethiopian movies legally. Upto 5 movies added daily. Here are the top 10 most viewed movies today.

Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።