የዕድሜ ባለጸጎችን ለመጦር የሚያስችለው የአምራች ዜጋ ቁጥር መመናመን ያስከተለው ሥጋት
አብዛኞቹ በይነ መንግሥታት በምርታማነት የሚፈረጀው ከ15-64 የዕድሜ ገደብ ውስጥ የሚካተተው ዜጋ ቁጥር ማሽቆልቆል እየገጠማቸው ነው። በዚህ የዕድሜ ክልል የሚገኘው ወጣት ከ65 ዓመት በላይ የሆናቸውን የዕድሜ ባለጸጎች ለመጦር ሃላፊነት የተጣለበት ሲሆን ቁጥሩ ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ መምጣቱ ዕርጅና የተጫናቸውን ዜጎች የረጅም ጊዜ የጤና እንክብካቤና የጡረታ ዋስትና አደጋ ላይ እንዳይጥለው ብርቱ ሥጋት አሳድሯል።
እ. ኤ.አ. በ1950 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ65ና ከዚያ በላይ ላለ ለእያንዳንዱ የዕድሜ ባለጸጋ በምርት ሂደት የሚሳተፉ 12 ሰዎች ነበሩ። ይህ አሃዝ በያዝነው 2010 ወደ 9 ያሽቆለቆለ ሲሆን በ2050 ደግሞ ወደ 4 ዝቅ እንደሚል ተገምቷል።
የዓለም ህዝብ ቆጠራ ቢሮ በ2010 ዓ.ም. ከ200 በላይ አገሮች ያሳተፈ የህዝብ ቆጠራ መረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን ጥናቱ 19 የሚደርሱ የህዝብ፣ የጤናና የአካባቢ አመላካች መሥፈርቶች ተካተውበታል። የዓለም ህዝበ ቆጠራ ቢሮ ፕሬዚደንት ቢልል ቡትዝ እንደሚሉት ከሆነ ጥናቱ የዓለም ህዝብ ሁለት አበይት አቅጣጫዎችን እየተከተለ ነው። በአንድ በኩል በበለጸጉ አገራት የወሊድ መጠን በእጅጉ መቀነስ ለዕድሜ ባለጸጋ ዜጎቻቸው ሊሰጥ የሚገባውን የጤና አገልግሎትና ሊኖራቸው የሚገባውን የመዋዕለ ንዋይ ዋስትና ክፉኛ እየተፈታተነው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በኢኮኖሚ ኋላ ቀር የሆኑ አገራት በህዝባቸው ቁጥር ላይ በያመቱ 80 ሚሊዮን ህዝብ እየጨመሩ ሲሆን እጅግ ድሃ ተብለው የተፈረጁት አገራት ዓመታዊ የህዝባቸው ዕድገት በ20 ሚሊዮን እየጋሸበ በመምጣቱ ድህነት እንድባባስና በተፈጥሮ ሃብት ላይ የተዛባ አጠቃቀም እንድከሰት ዋነኛ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
የዓለም ህዝብ ቁጥር በ2010 6.9 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ይህ የህዝብ ቁጥር ዕድገት ሊመጣ የቻለው በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ብቻ ነው ማለት ይቻላል።በአንጻሩ በዓለም በሚገኙ ሃብታም ሃገራት የሚኖረው የህዝብ ብዛት በአጠቃላይ 1.2 ቢሊዮን እንደሚደርስ ሲገመት የዕድሜ ባለጸጋ ቁጥሩ እየጨመረ፣ የምርታማው ዜጋ ቁጥር ደግሞ እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ነው። ለምሳሌ አንድት የጃፓን ሴት በአማካይ 1.4 ልጆች ሊኖራት እንደሚችል ሲታወቅ ይህ አሃዝ በጡረታ ክልል ከሚገኙ ዜጎቿ ጋር ሲሰላ 1ለ3 በመሆን በዓለም ጀርመንና ጣሊያንን ጨምሮ የመጨርሻው ረድፍ ላይ ያሰልፋታል። እ.ኤ.አ. በ2050 ጃፓን የአምራችና የጡረተኛ ስሌቱ 1ለ1 ጣሊያንና ጀርመን ደግሞ 1ለ2 ይሆናል።
የዓለም ህዝብ ቁጥር ከ5ቢሊዮን ወደ 6 ቢሊዮን ለመድረስ የፈጀበት ጊዜ 12 ዓመታት ብቻ ነው። በ2011 ደግሞ 7 ቢሊዮን ይደርሳል። “ጥያቄው 8 ቢሊዮን የሚደርሰው መቼ ነው?” የሚለው ይሆናል ይላሉ የሪፖርቱ አዘጋጅ ቢልል ቡትዝ። እንደሳቸው አገላለጽ የዓልም ህዝብ ቁጥር ይህን አሃዝ ምናልባት ከ13 ዓመታት በኋላ በ2024 ሊደርስበት ይችላል፤ ከዚያ ፈጥኖ ሊከሰት ግን አይችልም።
የ2010 የዓለም ህዝብ ቆጠራ ውጤት በበለጸጉና ደሃ አገራት መካከል ያለውን ንፅፅር በአሁኑ ጊዜ ተመሳሳይ የህዝብ ብዛት ያላቸውን ኢትዮጵያና ጀርመንን በምሳሌነት እንደሚከተለው አቅርቧል።
Key Demographic Indicators, 2010
Germany
|
Ethiopia
|
|
| Population mid-2010 | 82 million | 85 million |
| Population 2050 (projected) | 72 million | 174 million |
| Percent of population below age 15 | 14% | 44% |
| Percent of population ages 65+ | 20% | 3% |
| Elderly support ratio (2010) | 3 | 17 |
| Elderly support ratio (2050) | 2 | 11 |
| Lifetime births per woman | 1.3 | 5.4 |
| Annual births | 650,000 | 3.3 million |
| Annual deaths | 840,000 | 1 million |
| Life expectancy at birth | 80 years | 55 years |
| Infant mortality rate (per 1,000 live births) | 3.5 | 77 |
| Annual infant deaths | 2,250 | 250,000 |
የ2010 የዓለም ህዝብ ቆጠራ ውጤት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ክስተቶች ለመተንበይ አስችሏል፤
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የምጣኔ ሃብት ቀውስ ከበለጸጉ አገራት መካከል በአሜሪካና ስፔይን የወሊድ መጠን ከተለመደው ዝቅ እንድል ያደረገ ሲሆን የወሊድ ቁጥር ዕድገት እያንሰራራ በታየባቸው እንደ ኖርዌና ሩሲያ ደግሞ አሁንም ዕድገት እየታየ ቢሆንም ጭማሪዎን አዝጋሚ እንድሆን አድርጓል።
የአፍሪካ ህዝብ ቁጥር በ2050 በ ዕጥፍ በመጨመር 2 ቢሊዮን እንደሚደርስ ሲገመት አሁን የሚገኝበት የዕድገት ፍጥነት እንድገታ ካልተደረገ በስተቀር ከላይ የተገለጸው አሃዝ ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል ስጋት አለ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ 40 በመቶ ወይም 2.7 ቢሊዮን ህዝብ መሠረታዊ መጸዳጃ ቤት የለውም። ይህን መሠረታዊ አገልግሎት ለማግኘት ያልታደለው ህዝብ በአብዛኛው የገጠር ኗሪ ሲሆን መጸዳጃ ቤት የሚጠቀመው ህዝብ በመቶኛ ሲሰላ 40 በመቶ ብቻ ነው።
የዩናይተድ ስቴትስ አዛውንት ቁጥር እየጨመረ ስለሚሄድ የሶሻል ሰኩሪቲና የሜድኬር አገልግሎት ክፍያ በዕጅጉ እንደሚያሻቅብ ይጠበቃል። ስለሆነም በአሁነ ሰዓት ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ለመስጠት የሚመደበው የአገሪቱ GDP 8.4 በመቶ መዋዕለ ንዋይ በ2030 ወደ 12.5 በመቶ ከፍ እንደሚል የሚያሳየው ሪፖርት በዕድሜ ለገፉትም ሆነ ለአምራቹ ዜጋ ጥሩ ዜና አይደለም።
ትርጉም በወርቁ ሙላት
ምንጭ፡ Population Reference Bureau