ዲሞክራሲ በተግባር

የእንግሊዝ መንግሥት በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ አማካይነት በያመቱ የሀገሮችን የሰብዓዊ መብቶች አያያዝና ዲሞክራሲ ሪፖርት ያወጣል። በዚሁ መሠረት፥ ያለፈውን ማለትም እ አ አ የ 2014 ዓ ም ሪፖርት ባለፈው ሣምንት አውጥቷል። በዚህ 200 ግድም ገጾች ባሉት ሰፊ ሪፖርቱ፥ በተለይ የእንግሊዝን መንግሥት በብርቱ ያሳስባሉ ያላቸውን የ 27 ሀገሮች የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ገምግሟል። በ 27ቱ ሀገሮች ዝርዝር ውስጥ 8ቱ የኤርትራን ጨምሮ ከአፍሪካ ሲሆኑ፥ በተለይ የኢትዮጵያ መንግሥት የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን በማገድ ይተቻል። ​የዲሞክራሲ በተግባር ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ሰሎሞን ክፍሌ ለዛሬ በሁለቱ፥ ማለትም በኤርትራና በኢትዮጵያ ላይ የቀረበውን ሪፖርት ይመለከታል።