አበበ በለውና ኢካዴፍ – ግርማ ካሳ
በዚህ ሳምንት እና ባለፈው ሳምንት በሻእቢያ ዙሪያ ዉይይቱ ጦዟል። መቸም አበበ በለዉን የማውቀ የለም። በጣም የሚመቸኝ የርዲዮ ተንታኝ ነው። አንድ ሁለት ጊዜ በርሱ ራዲዮ ቀርቤ አስተያየት የሰጠሁበት ጊዜም አለ። እኔ እስከማወቀው ድረስ አበበ በለለው የግንቦት ሰባት እና የኢሳት ጠንካራ ደጋፊ ነው። ለኢሳት በአበበ በለዉና በታማኝ መካከል ምን ልዩነት የለም።
ሆኖም “ወያኔ ወያኔ ትሸታለህ” ተብሎ ዘመቻ ተጀምሮበታል። በተለይም የነ ፊታወራሪ እንደልቡ ኢካዴፍ ከረንት አፌር ክፍል አልተቻለም። ይቅርታ ይደረግልኝና በተለይም በዉጭው አለም ፖለቲካችንን የታመመ ነው። አንድ ሰው የተለየ ሐሳብ ካፈለቀ ያ ሰው ወያኔ ነው። ከዚህ በፊት የግንቦት ሰባትን ስትራቴጂዎች ተቃውሜ ስጽፍ፣ ልነግራችሁ አልችም ሲደርስ የነበረዉን ስድብ። አንድ ወቅት እንደዉም ወያኔ ተሻለ እስከማለት የደረስኩበት ሁኔታ ነበር።
እንደ ኢትዮጵያ ሜዲያ ያሉ ፈሪና አቋም የሌላቸው ድህረ ገጾችን እንደ ኢካዴፍ ያሉትን በመፍራት የምንልክላቸው ጽሁፎች ሁሌ የሚያወጡ የነበሩ ብሎክ እንድንደረግ ሆኗል። እንደዉም ኢትዮሜዲያ “ግርማ ካሳ የወያኔ ኤጀንት ነው” ብሎ ኤዲቶሪአል የጽፈበትም ሁኔታ አለ። ግርማ ካሳ ወያኔ ለመሆኑ ምንም መረጃ አለ ብትላቸው ግን የሚያቀርቡት ነገር የለም።
በጣም መማር ያለብን ይመስለኛል። መቻቻል መኖር አለበት። ተቃወምን ማለት ተቸን አምለት አይደለም። እኔ ከዞህ በፊት ግንቦት ሰባትን ስቃወም እጠላቸው ነበር ማለት አይደለም። ብዙዎቹን አወቃቸዋል። የሐሳብ ልዩነቶች አሉን እኔ በግልሰብ ደረጃ የማክበራቸው ናቸው። ትላንት ልዩነቶች ነበሩ ማለት ደግሞ ሁልጊዜ ይኖራሉ ማለት ላይሆን ይችላል። የአቋም መሸጋሸግ ሊመጣ ይችላል። ስለዚህ ዛሬ አልተስማማንም ብለን ፣ ነገ ልንስማም እንደምንችል ረስተን የግል ወዳጅነታችንን ማበላሸት የለብንም። መከባበር አለብን። ልዩነቶች ካሉ ደግሞ ላለመስማማት ተስማምትን እንቻቻል።
ለማንኛውም አበበ በላው በአንዳንድ ወገኖች በደረሰበት ትችትና ስድብ እንደማይደናገጥ አስባለሁ። እነኢዝህ ወገኖች ያው የኛ ወንድሞች ስለሆኑ በትእግስታችን ልናስተምራችው ይገባል።