የሚሊዮኖች ድምጽ – መደመጥ ያለበት ክርክር በመድበለ ፓርቲ ዙሪያ(ክፍል 1)
መድበለ ፓርቲ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ የለም – የሰማያዊና መድረክ ተከራካሪዎች
ሕወሃት በይስሙላው ምርጫ ደሞክራሲ አለ ለማስባል የመጀመሪያውን ክርክር አደርጓል። በክርክሩ ኢሕአዴግን ጨምሮ አምስት ድርጅቶች ተካፍለዋል። አትፓ (አዲስ ትዉልድ ፓርቲ) የሚባል አዲስ አበባ ዉስጥ የተወሰኑ ተመራጮችን ያስመዘገበ፣ ጠንካራውን ድርጅት ሕወሃት ምርጫ ቦርድን ተጠቅሞ ካገደ በኋላ ያቋቋመው የተለጣፊው አንድነትን እመራሉሁ ይለው ትግስቱ አወሉ፣ የብዙ ድርህቶች ስብስብ የሆነው መድረክ እንዲሁም በርካታ የአንድነት አባላትን እና ደጋፊዎችን ያቀፈው የሰማያዊ ፓርቲና ኢሕአዴግ ነበር የቀረቡት። በአጠቃላይ 5 ድርጅቶች።
ሆኖም ኢቢሲ በአጠቃላይ ለኢሕአዴግ 45 ደቂቃዎች ሲሰጥ፣ ለሌሎቹ ድርጅቶች ግን 19 ደቂቃዎች ብቻ ነበር የተሰጠው። በተሰጣቸው ጥቂት ደቂቃዎች ሕዝብ በብዛት የሚደግፋቸው መድረክ እና ሰማያዊ መሰረታዊ የሆኑ ነጥቦችን ያስቀመጡ ሲሆን፣ ሁለቱም የመድረበለ ፓርቲ ስርዓት በኢትዮጵያ እንደሌለ በይፋ ገልጸዋል።
መድረክ ወክለው የቀረቡት ዶር መራራ ኢሕአዴግ የሚያራምደው ፖለቲካ መድበለ ፓርቲ ዲሞኮራሲን በቀጥታ የሚጻረር ነው ብለዉታል። ዶር መራራ ፣ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር እንደመሆናቸው፣ ለመድበለ ፓርቲ ስር፤ዓት የሚይያስፈልጉ አምስት ነጥቦችን በመዘርዘ ፣ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ እነዚህ ነጥቦች እንደሌሉ ንው ለማሳየት የሞከሩት:
ኢንጂነር ይልቃል በበክላቸው መድበለ ፓርቲ ፖለቲካን ኢሕአዴግ እንደማያምን መረጃዎች በማቅረብ አስቀምጠዋል።
መድረክ እና ሰማያዊ በተሰጣቸው የመጀመሪያ ስድስት ስድስት ደቂቃዎች የተናገሩትን ይዳምጡ። ዶር መራራ እና ኢንጂነር ይልቃል የተናገሩት ለማዳመጥ 29.50 ደቂቃ ወደፊት መሄድ ይችላሉ።