በኦሮሚያ ፓርቲዎች ስሞታ እያሰሙ ነው – VOA

በኦሮሚያ ክልክ ደረጃ የተቋቋመው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት የሆኑ ስድስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥያቄዎቻችን ምላሽ አላገኙም በሚል ተሳትፏቸውን በጊዜአዊነት ማቋረጣቸውን አስታወቁ። የምርጫ ሥነ ምግባር ደንቡን በመፈረማችን እየተጠቀምን አይደለንም ሲሉ ፓርቲዎቹ እያማረሩ ነው። በ 2002 ዓም የተረቀቀውን የሥነ ምግባር ደንብ የፈረሙት እነዚሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ የምርጫ ወቅት በአባሎቻችን ላይ እየተፈጸመ ነው ላለው እንግልትና ወከባ መፍትሔ አላገኘንም ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል የገዥው ኢህአዴግ አባል ድርጅት ኦሕዴድ ወቀሳውን አስተባብሏል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

The post በኦሮሚያ ፓርቲዎች ስሞታ እያሰሙ ነው – VOA appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.