በእንግሊዝ ሃገር በለንደን ከተማ ከተመሠረተች 40 ዓመታትን ያስቆጠረችው ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ
ቀን፡ የካቲት 24/ 2007 ዓ/ም (03/03/2015)
በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሃዱ አምላክ አሜን!!
ባህረ ሐሰቱን የምንሻገርበትን የእውነት መርከብ ማን ይሰጠናል? ወዳጄ ሆይ፡- አትፍራ! እውነት አባትህ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዮሐ. 14÷6)፡፡ እርሱ ‹‹ መንገድም፣ እውነትም ፣ ሕይወትም ›› ነው፡፡ መንገድ ነው፡- ትሰማራበታለህ፣ እውነት ነው ፡-ትይዘዋለህ፣ ሕይወት ነው፡- ትኖረዋለህ !!!
በእግዚአብሔር ፍቃድና ቸርነት ይህቺን አንጋፋ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከመመሥረት አንስቶ አንድነታቸውን በማጠንከር ሃብትና ጉልበታቸው አፍሰሰው፤ ወጥተውና ወርደው፤ ጥረውና ግረው ያደረጇት፣ ኗሪነታቸው በእንግሊዝ ሃገር የሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ናቸው።
እነዚህ በሃይማኖታቸው፤ በኢትዮጵያዊ ታሪክና ባህላቸው ጸንተው የቆሙ የእንግሊዝ ሃገር ኗሪ ኢትዮጵያውያን በተለይ ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ለሥልጣን ከበቃበት ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ የጎሳ ፖለቲካውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለማስፈን የሚያደርገውን ጥረት በመቃወም በተለይም ደግሞ በዲያስፖራ የተመሠረቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትን በቀጥታና በተዘዋዋሪ ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነትን ለመከላከል ሲሉ በትግላቸውና በጥረታቸው የቤተ ክርስቲያናቸውን አስተዳደርም ሆነ ገንዘብና ንብረት በተመለከተ ያለማንም ጣልቃ ገብነት ቤተ ክርስቲያኗ ራሷን ችላ እንድትተዳደር በማድረግ ያለምንም ችግር ቤተ ክርስቲያናቸውን እያሳደጉና እያበለፀጉ፤ ወንጌልን እያስፋፉ በሰላም፤ በፍቅርና በጸጋ የሚኖሩ ነበሩ።
The post በእንግሊዝ ሃገር በለንደን ከተማ ከተመሠረተች 40 ዓመታትን ያስቆጠረችው ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.