ላፍታ ከሙላቱ አስታጥቄ ጋር (ክንፈ ሚካኤል)
ክንፈ ሚካኤል ( [email protected] )
ታላቁ መራሔ ሙዚቃ፣ አቀናባሪና ደራሲ ሙላቱ አስታጥቄ ባለፈው ወር መባቻ ላይ እንደ ዓመተ እግዚእ ከግንቦት 1 – 3 ምሽት እዚህ ሜልበርን ተዘጋጅቶ በነበረው ዓለም አቀፍ የጃዝ ሙዚቃ በዓል ላይ ተጋብዞ ለሦስት ቀን ከመክፈቻው ዕለት ግንቦት ቅዳሜ 1 ቀን 2 ሰዓት ገደማ ጀምሮ እሁድና ሰኞን ምሽት ጣዕም ያላቸውን የመሣሪያ ቅንብሮቹን ለታዳሚው አቅርቦ አስደስቷል።