የአዲስ አበባ የታክሲ ባለንብረቶች ቦንድ ካልገዛችሁ ታፔላ መውሰድ አትችሉም መባላቸውን ገለጹ።
በአዲስ አበባ በ10ሩም ክፈለ ከተሞች ለከተማው ነዋሪ የታክሲ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የታክሲ ባለንብረቶች እንደገለጹት ከሆነ በዛሬው እለት ታፔላ ለማሳደስ እና አዲስ ታፔላ ለማውጣት ወደመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣና ያቀኑት የታክሲ ባለንብረቶች እና ሹፌሮች ለአንድ ታፔላ የ500 ብር የአባይ ቦንድ ካልገዛቹህ ታፔላ አትወስዱም መባላቸውን ገልጸው በዚህም የተነሳ ባለንብረቶቹ ከመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ሰራተኖች ጋር ከፍተኛ እሰጣ እገባ ውስጥ የገቡ ሲሆን የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እኛ የምናውቀው ነገር የለም መመሪያው የመጣው ከላይ ነው እኛ የመጣላችሁን ስሩ ብቻ ነው የተባልነው በማለት ምልስ ሰጥተዋል።
ቦንድ ካልገዛችሁ ታፔላ አትውስዱም መባሉን ተከትሎ በዛሬው እለት በርካታ ታክሲዎች ከስራ ውጭ ሆነዋል ቦንድ ገዝተው ታፔላ የውሰዱት ባለታክሲዎችም ቢሆኑ ቁጥራቸው አነስተኛ በመሆኑ ለወትሮውም መጨናነቅ የሚታይበት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት በዛሬው እለት በባሰ ሁኔታ መጨናነቁን ክስፍራው ያገኘሁት መረጃ ያስረዳል።
The post የአዲስ አበባ የታክሲ ባለንብረቶች ቦንድ ካልገዛችሁ ታፔላ መውሰድ አትችሉም መባላቸውን ገለጹ። appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.