በቬጋስ የህብር ሬዲዮን 5ተኛ ዓመት ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ጎልድኮስት ሆቴል እንዲካሔድ ባለመፈቀዱ ወደ ሐምተን ኢን ሆቴል እንዲዛዋወር ተደረገ

ዛሬ ከላስቬጋስ አልፎ በመላው አለም ተደማጭ የሆነው የህብር ሬዲዮ፤ 5ተኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በመጭው ረቡዕ ፊብርዋሪ 25ቀን 2015 በቬጋስ ጎልድ ኮስት ሆቴል ያቀደውን ታላቅ ስብሰባ ሆቴሉ ረቡዕ ማካሄድ አይቻልም ብሎ በመሰረዙ፤ በዚያው በቬጋስ ወደሚገኘው ሐምፕተን ኢን ሆቴል በዕለቱ በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚያካሂድ የህብር ሬዲዮ ዝግጅት ክፍል ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ ገለፀ።

የአድዋ ድል 119ኛ ዓመት በሚዘከርበት፣ ወቅታዊ የአገር እና የጤና ጉዳይ ዋና መወያያ በሆነበት፣ በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ አቶ ኦባንግ ሜቶ ከካናዳ፣ የዘ-ሐበሻ ድህረ ገፅና ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሄኖክ አለማየሁ ከሚኒሶታ፣ እውቁ ዩሮሎጂስት ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን ከቬጋስ በሚገኙበት፤ አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የዓለም አቀፍ ፍትህ የኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዋና ስራ አስኪያጅ የሚሳተፉበትን ይህን ስብሰባ ሐሙስ እንጂ ረቡዕ ሊካሄድ አይችልም ሲል አስቀድሞ የተገባውን ውለታ አፍርሶ ዝግጅቱን ሰርዟል።በዚህ ከአቅማችን በላይ በሆነ ምክንያት የስብሰባውን ቦታ በዕለቱ በሐምተን ኢን ሆቴል ለማድረግ ተገደናል።

ጎልድ ኮስት ሆቴል ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ፌብርዋሪ 12/ 2015 በላከው የስልክ መልእክት የህብርን 5ተኛ ዓመት ዝግጅት የሰረዘ መሆኑን አሳውቀውናል። ከዚያ በኋላ በተደረገው ውይይት ረቡዕ ስብሰባው አለመደረጉ በህብር ላይ ጉዳት ያደርሳል ብለን ገልጸናል። በዚህ ሳቢያ ዝግጅቱን በመጭው ዕረቡ በቬጋስ ትሮፒካናና ዲን ማርቲን ላይ በሚገኘው ሐምፕተን ኢን ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድ የህብር ዝግጅት ክፍል ገልጿል።

የህብር ሬዲዮ 5ተኛ ዓመት በዋነኛነት የሚመጡ እንግዶች ባሉበት ስብሰባውን በተሳካ መንገድ ማድረግ ነው የወቅቱ ትኩረታችን የሚለው የህብር ሬዲዮ መግለጫ ባለፈው ዓመት በጎልድ ኮስት ሆቴል 4ተኛ ዓመታችንን ፌብርዋሪ 26/2014 በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን አስታውሷል።

ህብር ሬዲዮ የወቅታዊ መረጃ ምንጭ በመሆን በወቅታዊ አገራዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ፣በኢኮኖሚ፣ በጤና እና በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ላይ ሰፊ ትኩረት በመስጠት አቅም በቻለው መጠን የአማራጭ የሚዲያ ተግባሩን እያከናወነ መቆየቱን ይሔው መግለጫ ጠቅሶ ህ/ሰቡ በቬጋስና በአካባቢው የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወዳጆች በመጭው ረቡዕ ፌብርዋሪ 25 ቀን 2015 በ5 ፒኤም ትሮፒካናና ዲን ማርቲን ላይ በሚገኘው የሀምፕተን ኢን ሆቴል በሚካሄደው በዚህ ታላቅ ስብሰባ ላይ በመገኘት የተሳካ ዝግጅት እንዲደረግ የህብር ሬዲዮ አጋር እንዲሆኑ መግለጫው ጥሪውን አስተላልፏል።