ለማን ሃዉልት ይሰራ ለአጼ ዮሐነስ ወይስ ለመለስ ዜናዊ ? ግርማ
ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ታላላቅ መሪዎች መካከል አንዱ ታላቁ አጼ ዮሐንስ ናቸው። ስወዳቸው !!!! አጼ ዮሐንስ መቀሌ ላይ ሆነው ነበር ኢትዮጵያን ይገዙ የነበሩት። በርሳቸው ዘመን ኢትዮጵያ እጅግ በጣም ከባባድ ፈተናዎች ገጥመዋት ነበር። አረቦች ኢትዮጵያን የሃበሻ ምድር በሚል እንደ አረብ አገር ነበር የሚቆጥሯት። ግብጾችም የአባይን ምንጭ ለመቆጣጠርና የራሳቸው ለማድረግ ከጥንቱም ትልቅ ምኞት ነበራቸው። ለዚህም ነው ምኞታቸዉን ለማሳካት ሁለት ጊዜ ኢትዮጵያን የወረሩት ። በጉንደትና በጉራ በአጼ ዮሐንስ አዝማችነት ኢትዮጵያዉያን የግብጽን ጦር ድባቅ አደረጉት።ጣሊያኖችም አሰብ ላይ ተንጠልጥለው ወደ ተቀረው ኤርትራ ሊዘልቁ በነበረ ጊዜ፣ አዱሊስ ላይ (ምጽዋ አካባቢ ነው) በአጼ ዮሐነስ የባህር ምድሪ ( ኤርትራ) እንድራሴ በሆኑት በጀግናው ራስ አሉላ አባ ነጋ ከሚመራው ጦር ተፋልመው ጣሊያኖች ሽንፈት ደርሶባቸዋል።
መሃዲስቶች/ደርቡሾች (ሱዳኖች) ወደ ምእራብ ኢትዮኦያ በመዝለቅ አገራችንን በወረሩ ጊዜ (ጎንደር ከታማን ሁሉ ሳይቀር አቃጥለው ነበር)፣ አጼ ዮሐነስ በርሳቸው አዝማችነት ደርቡሾቹን ገፍቶ ለማስወጣት ችለዋል። የአጼ ዮሀንስ ጦር ደርቡሾችን እሰከ መተማ ገፍቶ ካስወጣ በኋላ፣ እንድ እፈሪ ከኋላ ኋላ የሚሆኑ ሳይሆን ፣ ከፊት እየቀደሙ የሚዋጉ መሪ ስለነበሩ፣ ከሩቅ በደርቡሾች በተተኮሰ ጥይት አጼ ዮሐንስ ይወድቅቃሉ። አጼ ዮሐነስ ለአገራቸዉን ለሕዝባቸው ሲፋለሙ ደማቸው መተማ ላይ ፈሰሰ።
አጼ ዪሐነስ ይዋሻሉ፣ መጠጥ አልጠጣም ይላሉ፤ ሲጠጡ አየናቸው በርግጥ፣ ራስ የሚያዞር መጠጥ” እንደሚለው ቅኔው፣ ደርቡሾች የአጼ ዮሐነስ አንገት ቆርጠው በከተሞቻቸው “የኢትዮጵያዉን ንጉስ ገደልን” ብለው በከተማዎቻቸው አዞሩ።
የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የትግራይ ሕዝብ፣ የመቀሌ ሕዝብ ይሄን ያውቃል። ታዲያ እኝህ ጀግና መሪ አንድ ሃዉልት ሳይኖራቸው (አክሱም አይሮፕላን ማረፊያው ከተሰራችህዋ ትንሿ ሃዉልት በስተቀር) ትላንት የመጣ፣ አገራችንን ባህር አልባ ያደረገ፣ ህዝባችንን በዘር የከፋፈለ፣ ብዙ ወገኖቻችን ያስገደለ፣ ያሳሰረ፣ ያሰቃየ፣ በደም ስክሮ የነበረን አምባገነን መሪ ሃዉልት በመቀሌ ከፍተኛ ተራራ ላይ ለማቆም መሞከር፣ የመቀሌ ፣ የትግራይ፣ የኢትዮጵያዉ ሕዝብ ለነጻነቱ የከፈለዉን መስዋትነት መናቅ አይደለምን ?
እስቲ ፍረዱ በመቀሌ ሃዉልት የሚገባው ለጀገናው አጼ ዮሐነስ ነው ወይስ ለመለስ ዜናዊ ? መለስ ዜናዊ ለመቀሌ ምን አደረገ ? መለስ ዜናዊ ለሕዙቡ ምን አደረገ ? የእነ ኦባማና እና ዴቪድ ካሜሮንን ጫማ እየላሰ ለምኖ መንገድና ፎቅ ስለሰራ ነው? እስቲ የቱ ሥራ ነው መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያዉያንን አስተባብሮ የገነባው ? እስቲ ንገሩኝ፣ ካለ ዉጭ እርዳታ የተሰራ ፕሮጀክት ? መንግስቱ ኃይለማሪያምም መለስ ያገኘውን የገንዘብ እርዳታ ቢያገኝ ኖሮ የተሻለ ሥር አይሰራም ነበርን ? አባይን የደፈረ የሚሉትም አሉ። አሁን ተግባራዊ የሆነው የአባይ ዲዛይን የተሰራው በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን አይደለምን ? እስቲ መለሳዉያን መከራከሪያ ካላችሁ መከራከሪያችሁን አቅርቡ።
አጼ ዮሐንስ ያደረጉትን ግን ማን ያደርጋል ? መንግስቱ ኃይለማሪያም ራሱ ሳይቀር ሲደነፋ እንዳልነበረ ፍርጥጦ ነው የሄደው። አጼ ኃይለስላሴም ቢሆኑ ሸሽተው ወደ እንግሊዝ ሄደዋል። አጼ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ፤ አጼ ዮሐነስ ደግሞ መተማ ላይ ጀግንነት ምንማለት እንደሆነ አሳይተዋል። በጎንደር የአጼ ቴዎድሮስ ሃዉልት አለ። በመቀሌ የአጼ ዮሀነስ ሃዉልት ነው መኖር ያለበት። አጼ ዮሐንስን የምትወዱ ሁሉ በቅርቡ ላዉንሽ የሚሆነው የሶሻል ሜዲያ በሶሻል ሜዲያ ላዉንች የሚሆነው ዘመቻ ዮሐንስን በመቀላቀል ፣ ሕወሃት ለመለስ ዜናዊ ሊሰራ ያሰበዉን ወደ አጼ ዮሐነስ እንዲቀይረው ግፊት አድርጉ። እናድርግ። በዚህ ዙሪያ ህዝቡን እናስተባብር።
በነገራችን ላይ አስቡት ሃዉልቱን ለማሰራት ሕወሃት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ያወጣል።፡በቅርብ ጊዜም የብሄር ብሄረሰብ በዓል ለማክበር በቤኔሻንጉል ወደ ሶስት መቶ ሚሊዮን ብር ጠፍቷል። ለባዶ ዳንኪራ !!!! የካቲ 11 ለሚከበረዉም የሕወሃት በዓል እንደዚሁ በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ገንዘብ እየጠፋ ነው። እንግዲህ የሕወሃት ትኩረት ምን እንደሆነ ተመልከቱ ። ያኔም ደርግ ለኢሰፓ በዓል ወዘተረፈ እያለ ሲያወጣ የነበረዉን ወጭ ስታዩ፣ አሁንም ህወሃት ዳግማዊ ደግም እንደዉም የባሰ መሆኑን በገሃድ እያሳየን ነው።
በዚህ ላጠቃልል በአለም ዋንጫ ጊዜ መቼም ሁላችንም የመድሃኔ አለም ሐዉልት በሪዮ ዴ ጃኔሮ ከፍታ ቦታ ላይ እናየው ነበር። አሁን የሕወሃት አላማ ከተሳካ የመለስ ዜናዊ ሐዉልት በመቀሌ ይተም ቦታ ብንሆን ልናየው ነው ማለት ነው። በናታችሁ …አይደብረም ?
—
The post ለማን ሃዉልት ይሰራ ለአጼ ዮሐነስ ወይስ ለመለስ ዜናዊ ? ግርማ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.