የአይቮሪኮስት ዝሆኖች ለዕሁዱ የዋንጫ ፍጻሜ አለፉ

የአይቮሪኮስት ዝሆኖች ትላንት ረቡዕ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክን ቡድን 3 ለ  1  በመርታት ለዕሁዱ የዋንጫ ፍጻሜ አለፉ።

 

የ 1992ቱ ሻምፒየን ከ 2012 ወዲህ ለዋንጫ ፍጻሜ ሲደርስ ይህ ሁለተኛው መሆኑ ነው።

 

የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ፈረንሣዊው Herve Renard በ 2012 ዛምቢያን ለሻምፒዮናነት ያደረሱ ሲሆን ዘንድሮ ዝሆኖቹ ካሸነፉ ሁለት ያፍሪካ ብሄራዊ ቲሞችን ለዋንጫ በማብቃት የመጀመሪያው ይሆናሉ።