የተቃዋሚ እጩዎችን በገንዘብ /በጥቅማጥቅም/ መደለል ሊጀመር ነው::
መጨውን የኢሕአዴግ የሞኖፖል ምርጫ ጥሪ ተቀብለው ወደ ምርጫ እንገባለን ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ያስመዘገቧቸውም እጩ ተወዳዳሪዎች አስፈላጊዉን ገንዘብ እና ጥቅማ ጥቅም በመስጠት የመደለል ስራ ሊጀመር ነው ሲሉ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ከኢሕአዴግ ጽ/ቤት የተገኙ መረጃዎች ጠቆሙ::የተቃዋሚ ድርጅቶች እያቀረቡ ያሉትን እጩዎች ስም እና ሙሉ አድራሻ ለኢሕአዴግ ጽ/ቤት የሚያስተላልፈው የገዢው ፓርቲ አጋር ተቋም የሆነው የምርጫ ቦርድ በክልል ወኪሎቹ እጮዎችን ከደህንነት አባላት ጋር በመሆን የማግባባት ስራ እንዲሰራ እና ከኢሕአዴግ ጽ/ቤትም አስፈላጊው በጀት ተመድቦ በሰፊው አፋጣኝ እንቅስቃሴ እንዲደረግ ተወስኗል::
አብዛኛዎች የብሄር ድርጅቶች ወደ ምክር ቤቱ እንዲገቡለት የሚፈጋው ኢሕአዴግ ለታማኝ ተቃዋሚው ኢዴፓ እና በመድረክ ፓርቲ ውስጥ ላሉ ተለጣጭ ወሬ አቀባይ ተለጣፊ አመራሮች ወንበር እንዳዘጋጀላቸው ታውቋል::የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት ዲፕሎማቶች ወያኔ ከተቃዋሚዎች ጋር እንዲወያይ እያደረጉ ያለው ጥረት አንድነትን በማፍረስ እና መኢአድን በመበጥበጥ ቀጣይ እኩይ ስራዎችን በመስራት ዲፕሎማቶቹ ያቀረቡትን ሃሳብ ለማጣመም ቢሰራም ወያኔ እንዳልተሳካለት ታውቋል::ወያኔ የሰራቸው ጸረ ተቃዋሚዎች እኩይ ተግባራት በዲፕሎማቶች ተቀባይነት አለማግኘቱ ታውቋል::
ሆዳሞችን እና አንሾካሻኪዎችን በዚህ በሰለጠነ ዘመን ላይ በመፍጠር የሚታወቀው የወያኔው ጉጀሌ ተጨማሪ አምስት አመታት በመግዛት ኢትዮጵያን ለመበታተን እና ሃግራዊ አንድነት እና ፍቅር ለማጥፋት ቢሰራም አልተሳካለትም:: እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚለው ወያኔ በአለም አቀፍ ደረጃ ወንጀሉ የታወቀለት እና በሕግ የሚፈለግ አሸባሪ ድርጅት መሆኑን የሚወጡ ዘገባዎች ሲያመለክቱ ኢትዮጵያውያን ሃገራችንን ከመንግስታዊ አሸባሪ ውድመት በጋራ ሁነን የመከላከል የዜግነት ግዴታ አለብን በማለት ለመናገር እወዳለሁ::
The post የተቃዋሚ እጩዎችን በገንዘብ /በጥቅማጥቅም/ መደለል ሊጀመር ነው:: appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.
