የማለዳ ወግ … የመረጃ አቅርቦቱ ተአማኒነት ፈተና ! -ነቢዩ ሲራክ

Nebiyu Sirak

ነቢዩ ሲራክ

* የአርቱስት ጌዲዮን ጉዳይ ካስተማረን

በማህበራዊ የመረጃ አቅርቦቱ የትስስር መድረክ በተለይም በ Facebook የሚሰራጩ ጭብጥ መረጃ የሌላቸው መረጃ ዎች information  አደገኛ እየሆኑ እየመጡ ነው ። በመረጃ የሚቀርቡትን የመረጃ ግንአቶች ጭምር አደጋ ላይ የጣሉበት ዋንኛ ምክንያት መረጃዎች ከሙያ ስነ ምግባር ውጭ በሚን ቀሳቀሱ ፣ በተለይም ሃላፊነት  በማይሰማቸው ወገኖች የሚለ ቀቁት መሆናቸው ነው ።  ይህም ጠቅለል ብሎ ሲታይ  ዘመነ ኛውን የመረጃ አቅርቦት ተአማኒነት ፈተና ላይ ጥሎታል ማለት ይቻላል።

ያለፈ የከረመውን የተሳሳተ መረጃ ስርጭት ትተን ባለፉት  ሁለት ቀናት የተሰራጩትን ሁለት መረጃዎች ብቻ ብንመለከት የተገኙት መረጃዎች ከየትም አቅጣጫ ይገኙ አስፈላጊውን ማጣራት ባለማድረግ በጥድፊያ  የሚወጡ መረጃዎችን አደ ጋኛነት ያመላክታሉ ። ከሶስት ቀናት በፊት ” ገጣሚ ታገል ሰይ ፉ በፖሊስ ተጠራ ” የሚለውና ትናንት ማምሻውን ” ታዳጊው አርቲስት ጌዲዮን ከፎቅ ላይ ወደቀ ” በሚል የተሰራጨው መ ረጃ ይጠቀሳል ። ዛሬ ስለ ገጣሚ ታገል ሰይፉ የተረጋገጠ ነገ ር ባይኖርም በታዳጊ ው በአርቲስት ጌዲዮን ዙሪያ የተሰራጨ ው መረጃ ግን ከእውነ ት የራቀና  መሰረተ ቢስተ መረጃ መሆ ኑ ታውቋል ።

በአርቲስት ጌዲዮን ከፎቅ ወደቀ በሚል የቀረበው በሬ ወ ለድ መረጃ የተላለፈው በታዋቂው የራዲዮ ጋዜጠኛ በአለምነ ህ ዋሴ የአዋዜ ዜና በብዙዎች አመኔታ ከሚሰጠው የመረጃ  ምንጭ የተገኘ ነው በሚል መረጃው በሰፊው ተሰራጭቶ ነበ ር። ያም ሆኖ መረጃው ፍጹም ያልሆነ መሆኑ ሲነገር የብዙዎቹ ን እምነት ሸርሽሯል ማለት ይቻላል ። በተፈጠረው የመረጃ ም ንጭ ግድፈት ዙሪያ ማብራሪያ የሰጠው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋ ሴ ” አርቲስት ጌዲዮን ከፎቅ ወደቀ!  !” የሚለውንም መረጃም ሆነ ዛሬ ” አርቲስት ጌዲዮን አልወደቀም ፣ ሰላም ነው  ” የሚ ለውን በመረጃ  ያቀበለው በመረጃ አቅርቦቱ ተአማኒነት አሳም ሮ የሚያውቀው የቁም ነገር መጽሔት አዘጋጅ መሆኑን አስታ ውቋል  ።

በጋዜጠኝነት የመረጃ አቅርቦት ስህተቶች ፈርጀ ብዙ በሆ ኑ ምክንያቶች ሊከሰቱ ይችላሉ።  ስህተቶች ሲከሰቱም ትክክ ለኛውን መረጃ በማቅረብ ስህተትን ማረም ተገቢና የሚጠበ ቅ ነው ። ያም ሆኖ ይህን ስህተቶች የተከሰቱት  መሰራት ያለባ ቸው ስራዎች ሳይሰሩ መሆኑ ሊያስተምረን ይገባል። በተጠቀ ሰው የአርቲስትጌዲዮን “ከፎቅ ወደቀ ” መረጃ አዲስ አበባ ው ስጥ ሆነ ከተባለ አዲስ አበባ ውስጥ ያሉትን ለምሳሌ አርቲስ ቱን አለያም የቤተሰብ አባላቱንም ሆነ ጓኞቹን ማነጋገርና ማረ ጋገጥ ተገቢ ነበር ።  ያ ካልሆነም ” ጌዲዮን ወደቀ ” ወደ ተባ ለበት ህንጻ ስልክ ደውሎም ሆነ በአካል ሄዶ ማጣራት አለመ ደረጉ ለበሬ ወለዱ ዜና መራገብ አንቱ የተባሉ ባለሙያዎች የ ሚጠበቅ ስህተት አልነበረም። ከሁሉም በላይ ያልታጣራውን ዜና እየተቀባበል ወሬውን ስናጦዝ ውለን ላደርነው ይህ ክስተ ት ካስተማረን በጎ ነገር ነው ።

አሁን አሁን ” ለመረጃ ቅርብ ነኝ !”  ለማለት ብቻ  የግብዝ ፉክክር በማህበረሰብ በማህበረሰቡ ሞራል ላይ ጉዳት ሊያ ፈርሱ የሚችሉ መረጃዎችን ሳያጣሩ በጥድፊያ የማሰራጨቱን አደጋ አስቀድሞ መቃኘት ከትልቅ ስህተት ሊያድነን ይችል ነበ ር።  በዚህ ረገድ ያለውን ችግር ለመቅረፍ በተለይ በጋዜጠኝ ነት ሙያ ላይ የተሰማራን ከአፍንጫችን ስር ያሉ መረጃዎች ሳ ናጣራ ተሯሩጠን ከማሰራጨት መቆጠቡ የመረጃ ፍሰቱን ተአ ማኒነት ያጎለብተዋል ። ተአማኒ ያልሆኑ መረጃዎች ለአመ ታት በትጋት የተገነባ መልካም ስም  ስም ፣ ዝና የሙያ ክህሎት ያ ጎድፈዋል ። በቅርብ ያሉ መረጃዎችን ቀርቶ በርቀትና ተደብቀ ው ያሉ መረጃዎችን በተቻለ መጠን ያላ ጥድፊያና እሽቅድድ ም ርቆ መረጃዎችን ቅርበት ካላቸው ምንጮች አጣርቶ ማቅረ ብ ተገቢ ነው ። ይህን ያለማድረጉ ዛሬ “መረጃዎቹ ትክክለኛ አይደሉም ” ሲ ባል ያጣውን የተአማኒነት አደጋ ማከም ቀላል እንዳይሆን አድ ርጎታል  !

በአርቲስት ጌዲዮን ዙሪያ የተለቀቁት ያልተጨበጡ መረጃ ዎች ሳይጣሩ የተሰራጩ መሆናቸው ግልጽ ሆኗል ። ይህም የመረጃውን በስህተት የማሰራጨቱን አንድ ጫፍ ” በይቅርታ ” ከማከሙ ባሻገር ለቀጣዩ ተአማኒ መረጃ አቅርቦት ጥንቃቄ እናደርግ ዘንድ አስተምሮት ከሆኑ እሰየው ነው !

መረጃ ህይዎት ነው ስንል  ሁሉም መረጃ ግን ትክክል ነው ማለት አለመሆኑን ልብ እንበል ። ከአቅም በላይ በሆነ ችግር  ስህተት ሲከሰትና ደግሞ ለስህተቱ አስፈላጊ ማብራሪያ ፣ እር ምትና ይቅርታ ተገቢ ነው !  መረጃ ህይዎት ነውና በተለይ ባለ ሙያዎች በቀዳሚነት መረጃዎችን በጥንቃቄ አጣትተን የማቅ ረብ ሃላፊነት አለብን !

ሰላም

ነቢዩ ሲራክ
ጥር 23 ቀን 2007 ዓም
Updated

The post የማለዳ ወግ … የመረጃ አቅርቦቱ ተአማኒነት ፈተና ! -ነቢዩ ሲራክ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.