የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም አጭር መልዕክት

ሕገ መንግሥቱና የመሰብሰብ፣ ሀሳብን የመግለጽና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶች

ከፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

እነዚህን መብቶች ከሕገ መንግሥቱ መፋቅ አንዱ መንገድ ነው፣ ወይም ኢሕአዴግ የሚሳነው የለምና የፖሊቲካ ፓርቲዎችን ሕግ በማንሣት ወያኔ/ኢሕአዴግ ብቸኛ ፓርቲ ሆኖ አገሩን መግዛት ይሻላል፤ በአንድ በኩል ሕገ መንግሥቱን ከነሰብአዊና ፖሊቲካ መብቶች እያወጁ በሌላ በኩል ሕጋዊ መብቶች ያሏቸው መስሏቸው ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡትን ወጣቶች በመሣሪያና በቆመጥ ጭንቅላቶቻቸውን እንደእባብ መቀጥቀጥ ምክንያቱ ምን ይሆን? የአውሬነት ጠባይ መሆኑ አያጠራጥርም፤ እስከመቼ?