የገነት ዘውዴ “ዶክትሬት” በህንድ ኒውዴልሂ
በህንድ ኒውዴልሂ ከተማ በሚገኘው ጄ.ኤን.ዩ (ጀበሃራል ነኸሩ ዩኒቨርሲቲ) በኢኮኖሚክስ ፒ.ኤች.ዲ ያገኘው አብዲ የወ/ሮ ገነት ዘውዴን የዶክትሬት ጥናት በመስራት እንዲመረቁ ማድረጉን ላረጋግጥ እወዳለሁ። በህንድ የነበርኩና ጉዳዩን በቅርብ ጠንቅቄ አውቃለሁ። አብዲ ከፍተኛ የትምህርት ችሎታ፣ እውቀትና ብቃት ያለው እንደሆነ ገነት ዘውዴ ጭምር ጠንቅቀው በማወቃቸው የእርሳቸውን የመመረቂያ ጥናቶች እንዲሰራ ካግባቡት በኋላ ጉዳዩ በሁለቱ መካከል እንዲቀር፣ ይህ ምስጢር ከወጣ ግን ሌላ ችግር አብዲ ላይ እንደሚከተል በማስጠንቀቅ ጭምር ነግረውታል።
ለአብዲ የቤት ኪራይና መሰል ወጪዎች በገነት ዘውዴ ይሸፈኑ ነበረ። በጣም የሚገርመው የመመረቂያ ጥናቱን ለዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰሮች ፕረዘንት ያደረገው አብዲ ነበር። በህንድ እንዲህ አይነት ኮራፕሽን የተለመደ በመሆኑ ብዙም አያስገርምም። በወቅቱ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች « በአብዲ ጭንቅላት ስር ገነት ካባ አጥልቃ ተመረቀች» ሲሉ ከመሳለቃቸው ባሻገር ድርጊቱን ወንጀል ነው ሲሉ ኮንነውታል።
በተለይ ወ/ሮ ገነት በህንድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ምክትላቸው ከነበረው የህወሀትና የደህንነት አባል ካህሳይ ገ/መድህን ጋር በመሆን የህንድ ሃብታሞችን ወደ ኢትዮጵያ በመላክና መሬት እንዲቀራመቱ በማድረግ ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን እንዲሁም ለዚህ ውለታቸው አብዲ የሰራውን ጥናት ወ/ሮ ገነት “ዶክተር” ተብለው እንዲመረቁ ተደርጓል።
ካህሳይ ገ/መድህን
The post የገነት ዘውዴ “ዶክትሬት” በህንድ ኒውዴልሂ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.