እቴጌ ጣይቱ እና ወይዘሮ ቀለሟ

በምስሉ ላይ ከእቴጌ ጣይቱ ጀረባ ቆመው የሚታዩት የንጉሳዊ ቤትሰብ የቅርብ ዘመድ፤ የአደዋ ጀግና፤ እና የእቴጌ ጣይቱ እስከዕለተ ቀብር ጓደኛ፤ ከጥንቷ ዳሞቴ ማሪያም ከአንኮብር አናት ላይ የሚቀዱት የትውልድ እና የእልፈት አመታቸው በትክክል ያልተመዘገበ በታሪክ ተጽፈው, ነገር ግን በትውልድ የተረሱት አንዴም ያልተዘመረላቸው ታሪካዊ እመቤት ወይዘሮ ቀለሟ አንድአርጌ ይባላሉ። በዚሁ ምስል ላይ ከፊት ለፊት የሚታየው ህጻን ልጅ እያሱ ሚካኤል ነው

Itege Taytu Wzr Kelemua and Iyasu Mikaelወይዘሮ ቀለሟ አጤ ምንሊክ በንጉሰ ነግስትነት በቆዩባቸው 24 አመታት በሙሉ ኑሮአቸውን በታላቁ ቤተመንግስት አድረገው የኖሩ እና ከንጉሱ ዕለተ እልፈትም በኋላ እቴጌ ጣይቱን አጅበው ወደ እንጦጦ ቤተመንግስት ተጉዘው ከእዛም እቴጌይቱ በህይወት በቆዩባቸው ስድስት አመታት አብረው ኖረዋል።

የወይዘሮ ቀለሟ የትዳር ታሪክ እና ስንት ልጆች እንደነበሮአቸው እኔ ይህን አጭር ታሪካቸውን ካገኘሁበት የጥሊያን ጦማር ላይ አልተጠቀሰም ነገር ግን በምንሊክ ዘመን ከነበሩት ባላባት ሴቶች በላይ የተማሩ እና የነቁ ስለነበሩ በአደዋ ጦርነት ጊዜም የእቴጌ ጣይቱ ,የጦር አማካሪ በመሆን ወደፍልሚያው ሜዳ አብረው ዘምተዋል። ዋና አላማዬ ለተዘመራላቸው እየደጋገሙ መዘመር ሳይሆን ፍጹም ከታሪክ ሰነድ ላይ የታፋቁትን ከትቢያ ጭሮ በማምጣት እንደገና ለዚህ ትውልድ ማስተዋወቅ ነው።

ጠንቋይ እቀልብ ይመስል ዘውትር በጓሮ ሰንዱቄ እባክህ ኤድ… ስለትላንቱ ትተህ ስለነገ ንገረን… ስለወደፊቱ ንገርን… እያለችሁ ለምትማጸኑኝ ወዳጆቼ, ታላቁ የህይወት መጽሀፍ “ሁሉም የዘራውን ያጭዳል” ብሎ እንዳስተማረው, እናንተም ዛሬ ቁምነገርን ከዘራችሁ ነገ ቁምነገርን ታጭዳላችሁ።

በምስሉ ላይ ከእቴጌ ጣይቱ ጀረባ ቆመው የሚታዩት የንጉሳዊ ቤትሰብ የቅርብ ዘመድ፤ የአደዋ ጀግና፤ እና የእቴጌ ጣይቱ እስከዕለተ ቀብር ጓደኛ፤ ከጥንቷ ዳሞቴ ማሪያም ከአንኮብር አናት ላይ የሚቀዱት የትውልድ እና የእልፈት አመታቸው በትክክል ያልተመዘገበ በታሪክ ተጽፈው, ነገር ግን በትውልድ የተረሱት አንዴም ያልተዘመረላቸው ታሪካዊ እመቤት ወይዘሮ ቀለሟ አንድአርጌ ይባላሉ። በዚሁ ምስል ላይ ከፊት ለፊት የሚታየው ህጻን ልጅ እያሱ ሚካኤል ነው።

ወይዘሮ ቀለሟ አጤ ምንሊክ በንጉሰ ነግስትነት በቆዩባቸው 24 አመታት በሙሉ ኑሮአቸውን በታላቁ ቤተመንግስት አድረገው የኖሩ እና ከንጉሱ ዕለተ እልፈትም በኋላ እቴጌ ጣይቱን አጅበው ወደ እንጦጦ ቤተመንግስት ተጉዘው ከእዛም እቴጌይቱ በህይወት በቆዩባቸው ስድስት አመታት አብረው ኖረዋል።

የወይዘሮ ቀለሟ የትዳር ታሪክ እና ስንት ልጆች እንደነበሮአቸው እኔ ይህን አጭር ታሪካቸውን ካገኘሁበት የጥሊያን ጦማር ላይ አልተጠቀሰም ነገር ግን በምንሊክ ዘመን ከነበሩት ባላባት ሴቶች በላይ የተማሩ እና የነቁ ስለነበሩ በአደዋ ጦርነት ጊዜም የእቴጌ ጣይቱ ,የጦር አማካሪ በመሆን ወደፍልሚያው ሜዳ አብረው ዘምተዋል። ዋና አላማዬ ለተዘመራላቸው እየደጋገሙ መዘመር ሳይሆን ፍጹም ከታሪክ ሰነድ ላይ የታፋቁትን ከትቢያ ጭሮ በማምጣት እንደገና ለዚህ ትውልድ ማስተዋወቅ ነው።

ጠንቋይ እቀልብ ይመስል ዘውትር በጓሮ ሰንዱቄ እባክህ ኤድ… ስለትላንቱ ትተህ ስለነገ ንገረን… ስለወደፊቱ ንገርን… እያለችሁ ለምትማጸኑኝ ወዳጆቼ, ታላቁ የህይወት መጽሀፍ “ሁሉም የዘራውን ያጭዳል” ብሎ እንዳስተማረው, እናንተም ዛሬ ቁምነገርን ከዘራችሁ ነገ ቁምነገርን ታጭዳላችሁ።”