የአንድነት አባላቶች እስር ቀጥሏል:: በአዲስ አበባ – ደብረማርቆስ – በሸዋሮቢት: በጋሞ ጎፋ ከተማ ቅስቀሳው ተጧጡፏል!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በነገው እለት በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያካሄድ ይታወቃል፡፡ በዛሬው እለት ፓርቲው በደብረማርቆስ ከተማ ነገ ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የደብረማርቆስ ህዝብ በቅስቀሳው ወቅት ጥሩ ግብረ-መልስ እየሰጠን ይገኛል፡፡ በነገው እለት ገዢው ፓርቲ አንድነትን ለማፍረስ የሸረበውን ሴራ እንደሚያወግዝ እየገለፀልን ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ፣ በከምባ ወረዳ፣ በሸዋሮቢትና ጂንካ በተመሳሳይ ሰዓት የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዳል፡፡ ስለሆነም ሁላችሁም በያላችሁበት ቦታ በመሆን አጋርነታችሁን እንድታሳዩ ፓርቲው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አንድነት የ23 ወረዳዎች የአዲስ አበባ መዋቅር የበራሪ ወረቀት ቅስቀሳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል ፡፡የአዲስ አበባ ምክር ቤት በፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት የተወሰነውን የማይቀለበስ ውሳኔ በማፅቅ አባላቱ ወደ ተግባር እንዲገቡ ባስተላለፈው መመሪያ በተጠንቀቅ የነበሩት 23ቱ ወረዳዎች በእኩል ሰዓት ቅስቀሳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡የአዲስ አበባ አባላት የተዘጋጀውን በራሪ ወረቀት ምክር ቤቱ ስብሰባ ከመግባቱ በፊት በየወረዳው አሰራጭተው የምክር ቤቱን ውሳኔ በትእግስት ይጠባበቁ እንደነበር እና ውሳኔው እንደተላለፈ ወደ ተግባር መግባታቸውን ለማወቅ ለችሏል፡፡ከማዕከል ይጀመራል ብለው የሚጠብቁ የደህነነት አካላት የሚይዙ የሚጨብጡትን አጥተዋል፡፡የአንድነት የትግል ስትራቴጂ ከኢህአዴግ የደህንነት መዋቅር በላይ መሆኑንም አመላክቷል፡፡udja1

udja14

udj-demp-Copy (1)

udj-demp-Copy (2)

udj-demp-Copy

udja9

udja3-Copy (1)

udja3-Copy