የአንድነት አመራሮችን ማሰር ተጀምሯል
1. አቶ አስራት አብርሃ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ
2. አቶ ሰለሞን ስዩም የፍኒትና ሚሊዮኖች ድምጽ ኤዲቶሪያል ሃላፊ
3. አቶ ስንታዩ ቸኮል የአዲስ አበባ ምክር ቤት የወጣቶች ክፍል ሃላፊ
4. አቶ ንዋይ ገበየሁ የህዝብ ግንኙነት ረዳት ሃላፊ እንዲሁም ሌሎችም ወደ አልታወቀ ቦታ በፖሊስ ተይዘው ተወሰደዋል።
ወያኔ/ኢሕአዴግ የኃይል የአዲስ አበባ ሰልፍ ከመደረጉ አንድ ቀን በፊት የኃይል እርምጃ መዉሰድ ጀምሯል። የአንድነት አመራሮች ፖሊስ እየጎተተ በማሳሰር እየሰራ ያለው፣ ከአቶ ትግስቱ አወል ጋር ከምርጫ ቦርድ ጋር አብሮ እየሰራ ያለው የማነ አሰፋ እንደሆነ ታወቋል።
በዚህ ሰዓት ትግሉ ወደ አንድ ምዕራፍ ተሸጋግሯል አአስራት፤ ነዋይ ፤ስንታየሁና ሰለሞን ቢታሰሩም እንኳ የሶሻል ሚዲያውን ከሀገር ውጪ ያሉ የአንድነት ምዕራፍ 2 ሶሻል ሚዲያ ቡድን አባላት እየመሩት ነው ምዕራፍ 3 እና 4 ከሰዓታት በኋላ የተጀመረው ትግል ግቡን እስኪመታ እረፍት አይኖራቸውም፡፡
Millions of voices for freedom – UDJ

The post በነትግስቱ ቡድን ጠቋሚነት የአንድነት አመራሮችን ማሰር ተጀምሯል appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.