ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ፣ በአዲስ አበባ ፣ በደብረ ማርቆስ ፣ በጂንካ ፣

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በደብረ ማርቆስ ፣ ጎጃም !!!

10933847_811306245608250_2534493435943277785_nሕወሃት/ኢሕአዴግ በአንድነት ፓርቲ ላይ የከፈተው ጦርነት ከመቼውም ጊዜ በአገሪቷ ያሉ ኢትዮጵያዉያን በቁጭትና በወኔ ለትግል እያነሳሳ ነው። በየክፍለ አገራቱ ያሉ የአንድነት አባላትን ደግፊዎች ድምጻቸውን ለማሰማት በመንቀስቀስ ላይ ናቸው። ጥር 17 ቀን በበርካታ ከተሞች ሰልፎች ይደረጋሉ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ደብረ ማርቆስም ድምጿን ታሰማለች። ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በደብረ ማርቆስ፣ ጎጃም !!!

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጂንካ ደቡብ ኦሞ (ጋሙጎፋ)

በአገሪቷ በሙሉ መዋቅር ያለውንና በምርጫ ሊያሸንፈኝ ይቻላል የሚለው ድርጅት፣ አንድነት ፓርቲ፣ ገዢው ፓርቲ ሕወሃት/ኢሕአዴግ በምርጫው እንዳይወዳደር የተለያየ መሰናክል በመፍጠር፣ በሚቆጣጠራቸው እንደ ኢቢሲና ራድዮ ፋና ባሉ ተቋማት ኢ-ሕገመንግስታዊ ዘመቻ ጀመሯል። ፓርቲው ተከፋፍሏል በሚል፣ ራሱ ላደራጃቸው ተለጣፊ ቡድኖችም እንደ “አንድነት” እውቅና ለመስጠት እየተዘጋጃ ያለ ይመስላል።

ሆኖም የአንድነት ፓርቲ፣ የሕዝብ ድርጅት እንጂ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ምርጫ ቦርድ የሚሰጠው ወረቀት ስላልሆነ ህዝቡ በአዲስ አበባን ጨምሮ በአገሪቷ ግዛቶች ሁሉ ድምጹን ያሰማ፣ ጥር 17 የሰላማዊ ሰለፎች ቀን ተብሎ ተወስኗል።

ሰልፍ ከሚደረግባቸው ከተሞች መካከል አንዱ በደቡክ ክልል በደቡም ኦሞ ዞን ያላቸው፣ ከአሥራ ሁለት በላይ ብሄረሰቦች መኖሩያ የሆነችዋ የጂንካ ከተማ ናት። ጂንካ ጥር 17 ቀን የለዉጥና የነጻነት ድምጿን ታሰማለች።

The post ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ፣ በአዲስ አበባ ፣ በደብረ ማርቆስ ፣ በጂንካ ፣ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.