ቅዱስ ገብርኤል ሥነ ባህርይን (ሞራልን) አከበረ!
ታላቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቅ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በተለያዩ ወቅታዊ ርዕሶች ላይ በተለይ ቤተክርስቲያን ተኮር የሆኑ በርካታ መጣጥፎችንና ትንተናዎችን ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በተለይም አብዛኛዎቹ የዘመናችን ካህናት ጌታችንና መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማምለክ ፋንታ ለባለ ነፍጦች ባደሩበትና በገበሩበት ፈታኝና አስተዛዛቢ ወቅት ቀሲስ አስተርአየና ሌሎች ጥቂት ሐቀኛ ካህናት በቤተክርስቲያንና በምዕመናን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ እንቅልፍ ነስቷቸው ለወገንና ለአገር ለመታደግ ከፍተና አርብርቦሽ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በዚህም መሠረት ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ፣ ሊቀ ማዕምራን ቀሲስ ዶ/ር አማረ ካሳዬና አባ ኃይለሚካኤል እ.አ.አ. ማርች 9, 2014 አሌክሳንደሪያ፣ ቨርጂኒያ ውስጥ በምትገኘው ሐመረ ኖህ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ታደሰ ሲሳይ የተባለ አወናባጅ ግለሰብ በፈጸመው የዝሙት ወንጀል ምክንያት ሥልጣነ ክህነቱን መግፈፋቸው ይታወሳል። እነዚህ አባቶች ሌሎች አድርባይና አስመሳይ አንዳንዶችም ግድየልሽ ካህናት የማይነኩትንና የማይቃጡትን ክርስቲያናዊ ሐዋርያ ያለው ሥራ በማከናወን እውነተኛ የካህንነት ተግባራቸውን በመውጣት ለወደፊት ትውልዶች በምሳሌነትና በትምህርትነት የሚጠቀስ ታላቅ ተግባር ፈጽመዋል። ቀሲስ አስተርአየ “ቅዱስ ገብርኤል ሥነ ባህርይን (ሞራልን) አከበረ!” በሚል ርዕስ የአገራችን ወቅታዊ ጉዳይ በሚመለከት ያዘጋጁልንን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ቅዱስ ገብርኤል ሞራልን አከበረ!