የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት አሁን ጠቅላላ ጉባኤ የምንጠራበት ምክንያት የለም ሲል ታሪካዊ ውሳኔ ወሰነ!
ባለፈው ቅዳሜ የተሰበሰበው የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ በፃፈው ድብዳቤ ከተወያየ በኋላ ደብዳቤው ህገወጥ ነው ሲል አወገዘ። ምርጫ ቦርድ ደማቅ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በተካሄደ ማግስት ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሩ ብሎ ሲያበቃ፤ ሲጠራ ደግሞ አልታዘብም ማለቱ ያስታወሱት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት አሁን ደግሞ ሌላ ለሶስተኛ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሩ ማለቱ ህገወጥ ተግባር ነው በማለት ከእንግዲህ ጠቅላላ ጉባኤ አንጠራም፤ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት እና ወደ ህዝቡ ነው የምንወስደው በማለት ወስኗል።
እንደዚሁም የአንድነት ስራ አስፈፃሚ በምርጫ ቦርድነ በስርዓቱ የተደቀነበትን የማፍረስ ዘመቻ ለመመከት ግብረ ኃይል ያቋቋመ ሲሆን ለጥር 17 ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድርግ እየተንቃቀሰ ይገኛል። በምንም ዓይነት ሁኔታ አንድነት ለምርጫ ቦርድ ህገወጥ ተግባራት አይምበረከክም፤ የምፅዓት ቀን ቀርበዋልና ለንሰሀ ተዘጋጁ እንዲል መፅሐፉ በምርጫው ይሳተፍም አይሳተፍም ህዝቡን ጫፍ እስከ ጫፍ የማደራቸቱን ስራ ግን ጠንክሮ እንደሚቀጥልበት የማያወላውል ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህ አጋጣሚ አንድነት ህዝባዊ ትግሉ ከፍ ወደ አለ ደረጃ ለማሸጋገር ያለው ታሪካዊ ሃላፊነት ለመወጣት ከመቸውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን እያሳወቀ አባላቱ፤ ደጋፊዎቹና ህዝቡ አመራሩ ለሚያሳልፈው ውሳኔና እንቅስቃሴ በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ ለማሳወቅ ይወዳል።
ድል የህዝብ ነው!
