ግድያ… በትግራይ!

በአምዶም ገብረስላሴ)

tigray-rebsha2-150x150በ2007 ዓ/ም የሚካሄድ ምርጫ ኣስፈፃሚ ምልሻዎች በመላ ትግራይ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የህወሓት ኣባላት ብቻ የሚመለመሉበት የትግራይ ምልሻ ምርጫው ከ99.6% ወደ 100 % ከፍ ላማድረግ የሚረዱ ተኳሽ ሚልሻዎች ከፍተኛ የተኩስ ልምምድ እያደረጉ ይገኛሉ። ስልጠናው ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በሗላ በዓይነቱ ለየት ያለና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የህወሓት ኣባላት ብቻ ምልሻዎች የተክስ ልምምድ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

ህወሓት ምርጫው እንከን የለሽና መቶ በመቶ ድምፁ ለራሱ ለማድረግ በሚያካሂደው ዘረፋ ሊያስፈፅሙ የሚችሉ ከህወሓት ኣባላት የሆኑ ምልምል የምርጫ ኣስፈፃሚ ኣባላት በተጨማሪ ኣልሞ ተኳሽ ሚሊሻዎች እያሰለጠነ ይገኛል።

የዚህ ስልጠና ኣካል የሆነ በኣፅቢ ወንበርታ ወረዳ ሓየሎም ቀበሌ ቓፀሎ በተባለ ስፍራ በ06 /05/ 2007 ዓ/ም ከሰልጣኞች በተተኮሰ ጥይት ኣቶ ሕሸ ገብሩ የተባለ ምልሻ በሰልጣኞቹ ሊገደል ችለዋል።

ኣቶ ሕሸ ገብሩ የ8 ልጆች ኣባት ነበሩ። በወረዳው እየሰለጠኑ የሚገኙ ሚልሻዎች ከኣቶ ሕሸ በተጨማሪ የቤትና የዱር እንስ ሳት እየገደሉ ይገኛሉ።
የምርጫ ኣስፈፃሚ ሚልሻዎቻችን የተሰጣቸው ግዳጅ ለታዘዙትም ላልታዘዙትም በመግደል ግዳጃቸው በኣግባቡ እንደሚዋጡ ኣሳይተዋል።

ምልሻ ዓወት ድራሩ ኣቶ ሕሽ ገብሩን በመግደል እቅዱን ለመተግበር ዝግጁነቱን ኣሳይተዋል።

ነብስ ኣቶ ሕሸ ይማር እንላለን።

The post ግድያ… በትግራይ! appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.