የሰማያዊ ፓርቲ ለ2007 ምርጫ ተወዳዳሪዎች እያስመዘገብ ነው ! – ስሜነህ ታዘበው
ስሜነህ ታዘበው/ ከአዲስ አበባ
የ2007 ምርጫ ሊደረግ የቀረው ሶስት ወራት አካባቢ ብቻ ነው። ምርጫ ቦርድ ባወጣው ሰለዴ መሰረት የታዛቢ ምርጫዎችን ያደረግ ሲሆን፣ ለተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም የምርጫ ምልክታቸውን ሰጥቷል። የዲሞክራሲ ተቋማት ገለልተኛ ባልሆኑበት ሁኔታ ምርጫዉን መሳተፍ የማይታሰብ ነው የሚል አቋም በሊቀመንበሩ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትና ሌሎች የአመራር አባላት ሲያንጸባርቅ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ፣ የዣንጥላ ምልክት የተሰጠው ሲሆን፣ በተለያዩ ወረዳዎችም ተወዳዳሪዎችን እያስመዘገበ ነው።
ሆኖም በአገሪቷ አንጋፋና ጠንካራ ከሚባሉ ድርጅቶች መካከል በቀዳሚነት በሚጠቀሱት በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ እንዲሁም በመኢአድ ላይ ምርጫ ቦርድ፣ ወደ ምርጫዉ እንዳይገቡ መሰናክሎችን እያስቀመጠ እንዳለ የሚገልጹ አካሄዶች እየታዩ ነው። በራዲዮ ፋና እና በኢትዮጵያ ቴሌቭዥንም መኢአድ እና አንድነት ላይ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ የተከፈተ ሲሆን፣ በተለይም በገንዘብ የተገዙ ጥቂቶችን በማስተባበርም፣ ለአንድነት ተለጣፊ “አንድነትን” በመመስረት ደፋ ቀና እየተባለ እንደሆነ እየታየ ነው።
(የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ እንዲሁ የኢሕአዴጉ ሬድውን ሁሴን ለመወዳደር ከምርጫ ቦርድ የተሰጣቸውን ካርዶች አያይዘናል)

The post የሰማያዊ ፓርቲ ለ2007 ምርጫ ተወዳዳሪዎች እያስመዘገብ ነው ! – ስሜነህ ታዘበው appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.