ወያኔ በፌዴራል ዱላ ሽባ እናደርግሃለን የሚለው ህዝብ ባባዶ እጆ ወያኔን ሽባ እያደረገው ነው:: – Minilik Salsawi
ህዝብን ያዘናጋ እየመሰለው የተዘናጋው ህዝብን ያፋጀ እየመሰለው ያፋቀረው ወያኔ እንደት እንደሚሳካለት ባለማወቁ እየዳከረ ነው::ህዝባዊ ጥያቄዎች እየበረቱበት የመጣው ወያኔ መላወሻ በማጣቱ የሚያደርገውን እስካለማወቅ ደርሷል:: ከእነዚህም ድንብርብሮች አንዱ ከአባቱ ሻእቢያ እንደወረሰው የፈጠራ ወሬ በአለም አቀፍ ደረጃ ማሰራጨት ነው:: እንዲሁም የህብረተሰቡን ጥያቄዎች ያስረሱልኛል ጭንቅላት ይሰርቃሉ የሚል እደምታ ያለውን ፈጣን ዘገባ ማሰራጨት ቅርሶችን እና የሃገር እና ሕዝብ አትኩሮት ይስባሉ የተባሉ ነገሮችን ማውደም የህዝብን አንግት ለመስበር እና ህዝብን ሃዘን ለማስቀመጥ ማለም ሃሳብን ሰርቆ አቅጣጫ በማስቀየር የማሰቢያ ጊዜ እንዲያገኝ መትጋት ስራዬ ብሎ ይዞታል::
ባለፉት 24 አመታት የአገዛዝ ዘመኑ ወያኔ ስልታዊ የሆኑ ያልሰለጠኑ እና ጫካዊ ብልሃቶችን ለመፍጠር እና ሲነቁበትም አለማቀፍ ሽብርን ይፈጥራሉ የሚለውን ወንጀል በዜጎች ላይ በመላከክ የትግል መሪ ሃሳቦችን ወደ አንድ አቅጣጫ ሊነዳቸው ይፈልጋል:: የህዝቦችን የመብት እና የነጻነት ጥያቄ መመለስ ያቃተው ወያኔ በሚፈጥራቸው የፈጠራ ወሬዎች ህዝቡን ለማደንዘዝ እና ለማዘናጋት እየዳከረ ይገኛል::የስርኣቱን ንዝህላልነት እና እየደከመ ለመውደቅ መንገዳገዱን እንዳያሳብቅበት ይመስላል የተለያየ ዘዴ በመፍጠር እና በማስወራት ራሱን ለትዝብት ዳርጓል:: ህዝብን አዘናጋለሁ ብሎ ራሱ በመዘናጋት በሽታ የተጠቃው ወያኔ ለህዝባዊ ጥያቄዎች መልስ ቢሰጥ የተሻለ ይሆናል:: የዛኔ ህዝብን ማዘናጋት ይቻላል::
የራሳቸው ደጋፊዎች እና ተቃዋሚ ዲያስፖራዎች በሃገር ውስጥ ያለው የሰብኣዊ መብት አያያዝ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች….. የኑሩ ውድነት የመዘዋወር መብት የሃይማኖት እና የህግ ጉዳይ ጥያቄዎችን አንግበው ተነስተውባታል ወያኔ ላይ:: በምንም ነገር ህዝብን በማዘናጋት ትግልን ለማሰልሰል የተደረጉ ሙከራዎች አይሳኩም ህዝባዊ ጥያቄዎች ሲመለሱ የዛን ጊዜ …የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ሲፈቱ ያን ሰአት …ህዝብ ጠግቦ ሲያድር…መልክም አስተዳደር ሲሰፍን ሰው በእውቀት ሲሰራ ጎሳ መቁጠር ሲቆም …ፍትሃዊ እና ነጻ ምርጫ በሃገሪቱ ሲሰፍን ጠላትነት እና የጎሳ ተኮር ፖለቲካ ሲወገድ የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ ሲኖር ፍርድ ቤቶች/ዳኞች ከመንግስት ባለስልጣናት መዳፍ ወተው በነጻነት ሲሰሩ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ሲመለሱ ህዝብ አርፎ ይቀመጣል::
የሙስሊሙ ሕብረተሰብ ጥያቄና የተቃውሞ ሰልፍ፣ የተቃዋሚወች ጫጫታ፣ የኢኮኖሚው ድቀት፣ የስራአጥነት ብዛት፣ የፖለቲካ ምሕዳሩን እንዲአሰፋና የዜጎችን መብት እንዲጠብቅ በምእራቡ ዓለም የሚደረግበት ግፊትና ተጽእኖ ወዘት ከአቢዮታዊ ዴሞካራሲ ጋር በቀጥታ የሚላተምበት ስለሆነ ብዙ ቅራኔ ውስጥ መግባቱ አያጠራጠርም:: በሰላም ሊአስገዛው የሚችል አይሆንም:: ተቃውሞው በዓይነት በመጠንና በስፋት እየጨመረበት ይሄዳል:: የህዝብ ተቃውሞ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የመንግስት አፈናም እይተባባሰ ይሄዳል::ይሕም ወደ ሕዝብ አመጽ ይሸጋገራል::ህዝባዊ ጥያቄዎች ታዝለው ግን ረዥም ማንገድ መሄድ አደጋ ስላለው የተዘናጋው ወያኔ በፌዴራል ዱላ ሽባ እናደርግሃለን የሚለው ህዝብ ባባዶ እጆ ወያኔን ሽባ እያደረገው ነው::