በነቀምቴ ከተማ አንድ እናት ሶስት ልጆችን ተገላግላለች

ኤፍ.ቢ.ሲ

በነቀምቴ ከተማ አንድ እናት ሶስት ልጆችን ተገላግላለች።

እናትዬው ሀዊ ጭምዴሳ ስትባል ከ25 አመት በላይ እንደሆነች ዘገባው ጠቅሷል።
እናትዬው ህፃናቱን የተገላገለችው ባሳለፍነው ሰኞ 

ሁለቱ የወንድ ፆታ ሲኖራቸው አንዷ ደግሞ ሴት ነች።

የሁለቱ ወንድ ህፃናት ክብደት እንድ ኪሎ ተኩል ሲሆን ሴቷ ደግሞ ሁለት ኪሎ ተኩል እንደምትመዝን ተገልፃል።

ህፃናቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና ወንዶቹም ቦንሳ እና ቦና እንዲሁም ሴቷ ቦንቱ በመባል መሰየማቸውን የነቀምቴ ፋና ኤፍ ኤም ባልደረባችን ብሌን ግርማቸው ዘግባለች።

Receive Ethiopian News and Videos by email. Sign up for Email alerts ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።