የኢትዮጵያውያን ነፃነት ለማስመለስ እስከደም ጠብታ ለመክፈል የተዘጋጀ የአንድነት አባል ውርጭና ብርድ አይበግረውም!!!

ለነዚህ የኢትዮጵያ ልጆች ክብር ይገባቸዋል!!!
እነዚህ በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው የአንድነት ጉባኤተኞች ከመላው የኢትዮጵያ ክልሎች በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ላይ በገዢው የኢህአዲግ መንግስትና በማደጎ ልጁ የምርጫ ቦርድ እንዲሁም ህሊናቸውን በገንዘብ ሽጠው አንድነትን ለመፈረካከስ ከተነሱ ጥቂት ሆድ አደር የማፊያ ቡድኖች እየተሰነዘረበት ያለውን ተከታታይና እልህ አስጨራሽ ደባ ለማክሸፍ በ24 ሰዓት ጥሪ ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው፤…… በአንድነት ፅ/ቤት በ03/05/07 ዓ.ም የሚካሄደውን ጉባኤ ለመታደም የአንድነት የክተት ጥሪ ቆራጥ ታጋዮች ናቸው፡፡ ….በፎቶዎቹ ላይ እንደምታዩት እነዚህ የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ ለመወሰን በመታገል ላይ ያሉ ሰላማዊ ታጋዮች፤ ……ቁርጥራጭ ወረቀትና ማዳበሪያ አንጥፈው፤…… ድንኳንና ማዳበሪያ ለብሰው፤….በቀዝቃዛው የአድስ አበባ አየር የሲሚንቶ ወለል ላይ በብርድ የሚጠበሱ ቆራጥ፤ለለውጥ የተነሱና ለኢትዮጵያውያን ክብር ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው ውርጭ የሚጠጡ፤……ኢህአዲግን እንቅልፍ አሳጥተው የሚያቃዡ ጀግኖቻችን ናቸው!!! ……በእውነት ሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
በኢትዮጵያውያን ህዝቦች ገንዘብ የኢህአዲግ ካድሬዎች በሊሙዚን መኪና እየተንፈላሰሱ፤……በአለም ላይ እጅግ የቅንጦት ሂወት በሚባል አኳኋን እየኖሩ፡፡ ……ውስኪና ቮድካ ጨብጠው ለቅጥረኞቻቸው በሚያስተላልፉት ቀጭን ትእዛዝ እልፍ የነፃነት አርበኞችን እያስገደሉ፤እያሳሰሩ፤እያሰደቱ…… በህዝብ ሀብት በሚንቀሳቀሰው የህዝብ ሚዲያዎች በቅንጦት ብቅ እያሉ የፍትህና ዴሞክራሲ ተረጋግጧል፤….ሀገሪቱ በሁለት ዲጂት አደገች….ምናምን እያሉ የሚደሰኩሩ አንባገነን የኢህአዲግ ባለስልጣናት ባሉበትና የኢትዮጵያውያንን ነፃነት በጠብ መንጃቸው ቁጥጥር ስር ያረጉትን ኢህአዲጋውያን፤…..ለመታገል ክብርና ነፃነታችንን ከአፈሙዛችሁ ስር ፈልቅቀን እናወጣለን ብለው በውርጭ ለሚጠበሱት የአንድነት አባላትና አመራሮች ስለእውነት የሚያስብ ሁሉ ክብርና አድናቆት ሊሰጣቸው ይገባል!!! ……ውድ የኢትዮጵያ እውነተኛ ልጆች!!! ….እመኑኝ አንድነትን ሊያቆመው የሚችል ሀይል የለም፡፡ ….የምንታገለው ምርጫን የመጨረሻ የትግል ሂደት አድርገን አይደለም፤…. በመሆኑም በነዚህ ብርቅዬ ታጋዮች ስም አንድነት ፓርቲ በተከታታይ ለሚወስናቸው ፖለቲካዊ ውሳኔዎችና የትግል ጥሪዎች አጋርነታችሁን እንድታረጋግጡ መልእክቴን አስተላልፋለሁ፡፡ ……በ2007 ኢህአዲግ የፈራው ለውጥ አይቀሬ ነው፤….ድል የህዝብ ይሆናል!!! ….ለለውጥ እንነሳ!!!10923522_435976543219250_5899138637215248249_n

10929976_435976659885905_7063202679654821879_n

10559726_435976746552563_1734583492566496101_n

10428627_759966307421639_3753389504227116176_n

10348602_435977186552519_1260948976355552876_n

10346525_435976806552557_6872474233828421189_n

64334_759966300754973_6395978200166176093_n

10410216_435976909885880_480015798899799081_n

10906498_759966310754972_3457821015692444450_n

10906448_435977053219199_1062570666388367165_n