የዓለም የነዳጅ ምርት መቀነሱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ቻለች
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከሚያዝያ 2001 ዓ.ም ወዲህ ዝቅተኛውን ዋጋ አስመዘገበ።
የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፉ ገበያ ከ50 የአሜሪካ ዶላር በታች ሆኖ መመዝገቡን ነው ቢቢሲ ያስነበበው።
የዓለም የምጣኔ ኃብት ዕድገት አዝጋሚነት የፈጠረውን የአውሮፓና በማደግ ላይ ያሉ አገራት የነዳጅ ፍላጎት መቀዛቀዝና የነዳጅ አቅርቦትን መጨመር ተከትሎ ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በማሽቆልቆል ላይ ይገኛል።
ሩስያ በታሪኳ ከፍተኛ የተባለውን 10 ነጥብ 667 ሚሊዮን በርሜል እያመረተች ሲሆን ኢራቅም በዚህ ወር ለውጭ ገበያ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ለመላክ አቅዳለች።
አሜሪካ በኖርዝ ዳኮታ ነዳጅ ከማውጣቷና በቀጣይም ምርቱ ሊጨምር ከመቻሉ ጋር ተዳምሮ የነዳጅ ዋጋ ከዚህም ሊወርድ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።
የነዳጅ ፍላጎትም ሆነ አቅርቦት በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የነዳጅ ዋጋ እስከ 40 የአሜሪካ ዶላር ሊወርድ እንደሚችል ተንታኞች ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ምንጭ፦ኢዜአ
Receive Ethiopian News and Videos by email. Sign up for Email alerts ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።