አንድነት ፓርቲ ከሜዲያዎች ጋር ያደረገው ቴሌኮንፍረንስ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!!

የአንድነት ሰሜን አሜሪካ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ባዘጋጀው የዛሬው ቴሌኮንፈራንስ የቴሌቭዥኝ ፣ የራዲዮ ጣቢያዎች፣ ድህረ ገጾችና ፓልቶክ ክፍሎች ተጋብዘዋል።
በዚህ መሰረት ማህደረ አድነት ( አትላንታ)፣ ሕብር ራዲዮ (ላስ ቬጋስ)፣ መለከተ ራዲዮ ( ቫንኮቨር)፣ የአንድነት ድምጽ ራዲዮ ( ዲሲ)፣ የአዲስ ድምጽ ራዲዮ (ዲሲ)፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች አንድነት ድምጽ ራዲዮ፣ አቡጊዳ፣ ሳተናው እና ዘሃበሻ ድህረ ገጾች፣ የቃሌ፣ የከረንት አፌር እና የሲቪሊቲ ፓልቶክ ክፍሎች ጥሪውን አክብረው በመገኘት ያሏቸውን ጥያቄዎች አቅርብዋል። ከሜዲያ ሰዎች በተጨማሪ በቴሌኮንፈራሱ የተገኙ ኢትዮጵያውያን በግለሰብ ደረጃ ለአንድነት መሪ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። አቶ በላይም ለተጠየቁ ጥያቄዎች በሙሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ዉይይቱ ከሁለት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ በላይ የፈጀ ሲሆን፣ የሰሜን አሜሪካ አስተባባሪዎች ይህ አይነት በሜዲያው በኩል ከሕዝብ ጋር የመወያየን ዝግጅቶች በተደጋጋሚ እንደሚያዘጋጁ አሳወቀዋል።
በተጨማሪም አቶ በላይ ፍቃዱ የአንድነት ፕሬዘዳንት በትናንትናው እለት በኢካዴፍ ፓልቶክ ክፍል ፤ አቶ ዳንኤል ተፈራ የአንድነት ውጭ ጉዳይ ሐላፊ ደግሞ በዪኢዲፎ ፓልትፕክ ክፍል ቀርበው ስለአንድነት ገለጻ ማድርጋቸው ታውቋል። በዚህም ውይይት ላይ አንድነት ስላለበት ሁኔታ እና መጪውን ምርጫ 2007 አስመልከቶ በአለም ዙሪያ ሁሉ ላሉ ኢትዮጵያዉያን ማብራሪያ ሰጥተዋል፣ በተለያዩ አርእስቶች ዙሪያ ከፓልቶክ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።

የአንድነት የዉጭ ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ተፈራ በዮናይትድ ኢትዮጵያን ዲስከሽን ፎረም ሲቀርቡ የአንድነት ሊቀመንበር አቶ በላይ ፍቃዱ በኢካዴፍ ሩም ነበር ገለጻ የሰጡት።
አቶ በላይ ፍቃደ አንድነት እያደረጋቸው ስላለው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴውች ካብራሩ በኋላ፣ በቀዳሚነት፣ ከክፍሉ አድሚኖች መካከል አንዷ በሆኑት በሙያዬ ምስክር የተጠየቁት፣ አንድነት ከትብብር ጋር አብሮ አብሮ ለምስን አይስራም የሚል ጥያቄ ነበር።

የትብብርና የአንድነትን አስፈላጊነት ካሰመርበት በኋላ አንድነት ትብብር ዉስጥ ገብቶ አብሮ ለመስራት ችግር እንደሌለበትና ፍቃደኛ እንደሆነ የገለጹት አቶ በላይ፣ አንድንት እና ትብብር ውስጥ ያሉ ደርጅቶች አሁን መዋሃድ ባይቻሉም ፣ በሂደት ግን የመዋሃድ ኮሚትመንት ሊኖራቸው እንደሚገባም አስረድተዋል። ያ ባልሆነበት ሁኔት ለጊዜው ተብሎ የሚደረግ ትብብር በመድረክ የነበረዉን ሁኔታ መድገም እንደሆነ አቶ በላይ ሳይጠቅሱ አላለፉም።

አላማ111 የተባሉ የክፍሉ ታዳሚ “ምን ያህል ጽ/ቤት አንድነት እንዳለው ሊገልጹልን ይችላሉ ? ከመድረክ ፣ ከመኢአድ ከሰማያዊ ፓርቲ ያለውን ልዩነት ለመፍታት አንድነት እቅድ አለው ወይ ?” በማለት ለጠየቅት ጥያቄ፣ አቶ በላይ ሲመልሱ በመድረክ ዉስጥ ካሉ ደርጅቶች ጋር አንድነት ወደ ዉህደት እንዲኬድ ብዙ ጥረት እንዳደረገ ገልጸው፣ ያ ባለመሆኑ ከመድረክ ጋር ውህደት ሳይሆን፣ በትብብር የመስራት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል አስረድተዋል። መኢአድን በተመለከተ፣ “በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ምንም ችግር የለም። ወደ ክልሎቹ ብትሄዱ የአንድነት እና የመኢአድ አባላትን ለመለየት አይቻልም” ያሉት አቶ በላይ በመኢአድ እና በአንድነት አመራሮች መካከልም ጥሩ የሆነ ግንኙነት እንዳለ አስረድተዋል። አቶ በላይ ፣ በሰሜን ጎንደር የአንድነት እና መኢአድ አባላት አንድነትንና ትስስርን አቶ በላይ እንደ ምሳሌ አቅርበዋል።

ሰማያዊን በተመለከተ “የሰማያዊ አባላት ከአንድነት የመጡ እንደመሆኑ፣ በሂደት የመጡ ችግሮች ነበሩ። ትግሉን ወደፊት ለመግፋት ግን የታሪክ እስረኛ መሆን የለብንም። ፎርዋርድ ሉኪንግ ሆነን ወደፊት መሄድ አለብን” ያሉት አቶ በላይ፣ የሰማያዊ አመራሮችን ብዙዎቹን እንደሚያወቋቸው፣ የልብ ጓደኞቻቸው ወዳጆቻቸው እንደሆኑ ገልጸዋል። “የበለጠ አንድ ሆነን እንዳንሰራ ያደረገን መሰበር ያለበት፣ መደፈን ያለበት ጉድጓድ ያለ ይምሰለኛል። ያንን ከዘለልን የተሻለ ሁኔታ ልንሰራ እንችላለን። “ ሲሉ አቶ በላይ በአንድነት እና በሰማያዊ/ትብብር በኩል ያለው ግንኙነት የበለጠ ሊጠናከር እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ከአንድነት አመራሮች አካባቢ ስለ ኢሳት የተሰጡ አስተያየቶች በተመለከተ፣ ፖምፒዱ ከተባሉ ታዳሚ የተጠየቁት አቶ በላይ “አንድነት እንደ ተቋምም ለኢሳት ከፍተኛ ቦታ ነው የሚሰጠው። ኢሳት ዉስጥ ያሉ ወንድሞች፣ ከፍተኛ ችግር ላይ ሆነው እየተረባረቡ ለሚሰሩት ሥራ አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ የሆነ አክብሮት ነው ያለው” የሚል ምላሽ ነው የሰጡት። “ኢሳት እንደተቋም አንዳንድ ከፍተቶች ካሉት፣ ኢሳትን መተቸት ችግር የለውም” ያሉት አቶ በላይ፣ ትችቱ ግን ኢሳትን የሚያጥላላና የሚያንበርከርክ ሳይሆን የሚያረም መሆን እንዳለበት ሳይጠቁሙ አላለፉም። በኢሳት ዙሪያ ከአንድነት አመራሮች የተሰጡት አስተያየቶች “ኢሳት ይሄን፣ ያን ቢያስተካከል “ በሚል እንደህፕንም አቶ በላይ አስረድተዋል።10153833_587630041337455_4078181881316786241_n