ዓለም አቀፍ ችግር እየሆነ የመጣዉ የግብር ማጭበርበር

ከጥቂት ወራት ወዲህ አንድ የተደበቀ ነገር ግልፅ እየሆነ መጥቷል። ይኸዉም በርካታ ትላልቅ ኩባንያዎች እና የንግድ ድርጅቶች ለመንግሥት በሕጉ መሠረት ገቢ ማድረግ የሚገባቸዉን ግብር ላለመክፈል በስዉር ያሸሻሉ ተብለዉ በብዙ ሃገራት ተከሰዋል።