አንድነት ለሕዝቡና ለትግሉ ኃላፊነት የሚሰማው ድርጅት ነው (ምርጫን በተመለከተ) – ናኦሚ

ምንም እንኳን የፖለቲካ ምህዳሩ የጠበበ ብቻ ሳይሆን የተዘጋ ቢሆንም፣ የአንድነት ፓርቲ በምርጫ 2007 እንደሚወዳደር በይፋ ለሕዝብ ማሳወቁ ይታወቃል። አንዳንድ ወገኖች “አንድነት እንዴት ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ ይገባል ?” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። እነዚህ ወገኖች ይሄን ጥያቄ ለምን እንዳቀረቡ ግልጽ ቢሆንም፣ ወድ ምርጫው አለመግባቱ ደግሞ ሊያስከትል የሚችለው የራሱ ጉዳት እንደሚኖር የመረዳት ችግር ያለ ይመስላል። በተለይም በፖለኢትካው ብዙ የሚሳተፉ፣ ጋዜጠኞች አንድ ዉሳኔ ሲቃወሙ፣ ሌላውን ዉሳኔ መመርመር አለመቻላቸው ብዙዎችን እያስገረመ ነው።

አንድነት በስሜትና በጀብደኝነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፣ አቅሙን በሚገባ ገምግሞ፣ የሚጠቅመውን እና የሚጎዳዉን አመዛዝኖ፣ ሰፊ ዉይይትና ምክክር አድርጎ ዉሳኔዎችን የሚወስን፣ ለሕዝቡና ለትግሉ ኃላፊነት የሚሰማው ድርጅት ነው። አንድ ዉሳኔ ሲወሰን ጥቅሙና ጉዳቱን አስቀድሞ በመመርመር ነው።

አንድነት ወደ ምርጫው እንደሚገባ ሲያሳውቅ፣ ወደ ምርጫ አለመግባቱ ሊያመጣ የሚችለውን ጥቅምና ጉዳት አስቀድሞ በሚገባ ጥናት አድርጎበት ነው።

አንድነት ወደ ምርጫዉ መግባት እንደሌለበት የሚከራከሩ ወገኖች የሚያቀርቡት አማራጭ ካለ፣ ወይንም “ምርጫዉን ባለመሳተፍ የሚገኝ ጥቅም አለ” ካሉ የሚገኙ ጥቅሞችን ለማሳየት ቢሞክሩ፣ አንድነት የሚያቀርቡትን መከራከሪያዎች አይቶ፣ ህዝብን እና ትግሉን እስከጠቀመ ድረስ ዉሳኔውን እንደገና የማይመለከትበት ምንም ምክንያት አይኖርም።

የአንድነት ዉሳኔ ትክክለኛ ዉሳኔ መሆኑን ለማየት በአለማችን የተደረጉ፣ የተለያዩ ቦይኮቶች ያመጡት ጉዳትና ጥቅም በማየት፣ በጥናት ላይ የተመሰረተ መረጃ ከዚህ በታች ማግኘት ይችላል።

http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=90014