ተርቲብ፤ አላህ ዋአክበር ናፈቀኝ።
በእርግጥም “ እንዲህ እንደዋዛ ሲጠሩት ቀላል ይመስላል ቃሉ፤ እረ ሁላችሁም፤ አገር አገር በሉ፤ አገር አገር በሉ”። የምትለዋ ስንኝ በጋራ ስንላት ንዝረቷ ለጉድ ነበር። ተመኩሮዬን ያኔ ቆርጦ ሰልፉ ላይ የነበረ በቅርብ ፅፎ አስታወሰኝ። “ተርቲብ” የምትለዋን ቃል ትርጉም እስካሁን ስለማላውቅ ሙሉ መልክቱን በእርግጥ በትክክል አልረዳውም። ያም ሆኖ “ተርቲብ፤ አላህ ዋአክበር”። በጋራ ስትሉት ሲያምር። ምጥን ያለና ጉልበታም ነበር። በሗላ በሗላ ህዝባዊ ሰልፋችሁ ላይ ሳልሰማው ስቀር ሁሉ ቅር ይለኝ ነበር።
19ኛው ም/ዓ የፈረንሳይ ህዝብ ሰቆቃ የሚያሳየው 2012 የወጣው Les miserable የሚለው ፊልም ላይ ተጨቋኝ እንቢተኞች በጋራ እየተቀባበሉ የሚሉት ዜማ የማይረሳና ድንቅ ኪነጥበብ ነው። የሰው ልጆች ከፈላጭ ቆራጮች ጋር ሲያደርጉ በነበረው ትግል የሙዚቃና የስነ ግጥም ጥበብ እንዴት ሲጠቀሙበት እንደነበር አጉልቶ ያሳያል። በዚህና በቀጣዩ አመት ከወጡት ፊልሞች ውስጥ በ2012 የወጣውን Django Unchained ዋና አክተሩ Jamie Foxx,እና 12 Years a Slave ሊታዩ የሚገባቸውና ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ናቸው።
አንድ አይነት በጋራ ልንላት የምንችል ስንኝ ለመስራት ሞክሬ፤ ሞክሬ አቃተኝ። የተለያዩ ብሄረሰቦችን ዜማ ሁሉ አዳመጥኩ። መልክቱን ከኔ። ዜማ ተውሼ ለሞሞከር ነበር። ያም ሆኖ እንኳ ላልተሰጠው ጉዳዩ መቼ ቀላል ሆኖ። አንድ ችግር ለብቻ ሲባልና በጋራ ሲባል የመልእክቱ ጥንካሬና ውበቱን ለማየት ከባድ እየሆነም መሰለኝ። ለማንኛውም በአይምሮዬ ስለነበረም ይሆናል ሀብታሙ አያሌው አሳምሮ የፍላጎቴን ሞላው። እመኑኙ ይወድቃል እያለ ሲያወርደው እጅጉኑ የሚያምርና ጠንካራ ነበር። ከነብስ ጋር ሄዶ የሚጣበቅ አይነት። ስሰራም፤ ስነዳም ለብቻዬ እዘምረዋለው። ደግሞ በቀላሉ የትኛውንም አይነት ሀሳብን ለመግልፅ ሲያመች።
አስር ሲያስሩ። ሐያ እንሆናለን።
መቶ ሲያስሩ። አንድ ሺ እንሆናለን።
እመኑኝ ይወድቃል።
አዎ ይወድቃል።
እናንተ ግን፤
እናንተ ግን።
ግደሉ፤ሲሏችሁ።
ህዝባችንን?። ለምን ሲባል?።
በሉት።
እናንተ ግን፤
እናንተ ግን።
ንፁሀንን?። ደሀዎችን?። ችግርህ ነው።በሉት።
ይወድቃል።
እመኑኝ ይወድቃል።
“ተርቲብ፤ አላህ ዋ ክበር”። አብዝቶ የሚታሰበኝና የሚናፍቀኝ ከውበቱ በተጨማሪ ከስሌት አኳያም ነው። እንደምናውቀው ትግል ያለ ስሌት ልፋት ነው። ጊዜ ቦታና ሁኔታዎችን አካቶ ማስላት አሸነፊ ለመሆን ወሳኝ ነው። የስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቼ በያዛችሁት ታሪካዊ ትግል ላይ ቀይ ካርድ መስጫው ጊዜ አሁን ይመስለኛል። ጫወታው በካርድ የሚሆንበት ጊዜ ላይ ደርሰናላ። አሁን ጥያቄያችንን መልስ አትመልስ፤ ፍታ አትፍታ አይደለም። ያ አለፈበት። ለጊዜው እንዲህ ብላችሁ አትጠይቁት። አንተ ትወርዳለህ እነሱ ይመልሱታል፤ አንተ ስትወርድ ያኔ ይፈታሉ ነው መባል ያለበት። ይህን ቀይ ካርድም ይዞ ይሁን ነጭ ወረቀት። ጥቁርም ለብሶ ይሁን ነጭ ጀለብያ። ተጮሆም ይሁን ተቀምጦ ብቻ በሆነ መንገድ ካሁኑ በዛ ብዛት እየወጡ ደግሞ ደጋግሞ ሊነገረውና ለሌሎችም ግልፅ መደረግ ያለበት ነው።
ከዚህ በሗላ አንመርጥህም፤ አንመርጠውም የሚለው ነው አላማ መሆን ያለበት። የምርጫ ጫወታ እንጫወት ያለው እሱ ነው። ዱላ ይዞ ምርጫ መሆን ደግሞ አይቻልም። መሰንዘሩ ግን አይቀርም። ቢሰነዝርም ዱላው እየነጠረ እራሱኑ አናት አናቱን ደግሞ ይለዋል። ስለዚህም በመጨረሻ ይወድቃል።
ማንም በማይክደው ትግላችሁ በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የአገራችን ታሪክ ጠንካራ፤ ፈር ቀዳጅና አስተማሪ አድርጎ መዝግቦታል። አሁንም ታሪካዊ ቦታውን እንደያዘ ይቀጥል። ይህን የምለው ሙሉ በሙሉ ብደግፈውም ስለናነተ ጥያቄና ትግል ብቻ አይደለም። እናንተ ባደባባይ አሁን አንመርጥህም ስትሉ በተመሳሳይ ባደባባይና በሚታይ አንመርጥህም የሚሉ ብዙዎች ይሆናሉ። በተንገሸገሽን ዜጎች ዘንድ ውይ በጣም እናዝናል!! እወቀው አንመርጥህም ፋሽን ይሆናል። እስከመቼ ለሁለት ተከፍለን፤ ሰላም አጥተንና ተዘባናችሁብን ያሉ ምርጫችን አይደለህም ሲሉ ነጭ ተለበሶ የሚኬድበት ቢታ ጥቁር ላብሰው ይሄዳሉ። የገበሬ አባቶቻችን መሬት ያሉ እንደምንም ተጠናክራችሁ ምርጫችን አይደለህም ሲትሉ አዋራው እስኪቦን በድጋሚ መሬት መምቻው ጊዜ አሁን ነው። ከዚህ ውጣ ከዚህ ግባ እየተባለ የተማረረውም ዜጋ አንመርጥህም ሲል የመጀመርያ ረድፈኛ አሁን መሆኑ ግድ ይለዋል። አለቃ ተሾሞላችሗል ግን ዛሬም ተክላይ ተክሉ ነገም ተክላይ ተክሉ ይህን ማየትና መስማት ስልችት ያላችሁ ምርጫችን አይደለህም ስትሉ ወደ ሰማይም ቢሆን መተኮሱ ይቆይና የስቢል ልብስ ለአንድ ቀን ብትለብሱስ። ግደሉ የሚል መመርያ ሲያወርድ የሚገድል አይኖርም ማለት አይደል?። ብቻ ሁላችንም የግድ ልናደርገው የሚገባ ፍቱን የሆነው መዳሀኒት አሁኑኑ በጋራ ምርጫችን አይደለህም ማለቱ ነው። ከቱንዚያው አቢዬት በፊት ሁላችንም ባንሆንም በብዙዎች በአንድ ተሆኖ በሚሊዬኖች እንቢኝ ማለቱ ዋና ነፃነትን ማግኛ መንገድ ነው ይሉ ነበር። ዘሬ ተቀባዩነቱ እያደገ ከመሄዱም በላይ ለዚህ ምቹ ሁኔታዎች እየበዙ የሄዱበት ነው። እንዴት መጀመርና መጨረስ እንዳለብንም የተሰላ ነው።
ተርቲብ፤ ብያለው። ጀምሮ እግማሽ ላይ ማቆም ትክክል ነው ካላላችሁ የእስልምና እምነት ተከታዬች ተቀበሉኝ።
ያለ አግባብ የሰራችሗቸውን በሙሉ አሁኗኑ ፍቱ።
ዳዊት ዳባ።
Saturday, November 29, 2014
[email protected]