ሁለት ዓይነት እንባ፤ ኃይሌም አለቀሰ።

ሕዝቡ ዛሬም ሲሞት፦
ደሙ እየፈሰሰ፤
ሁለት ዓይነት እንባ፦
ኃይሌም አለቀሰ።
የመጀመሪያው እምባ፦
ያኔ ጉንግን ሲያጠልቅ፤
በድል አድራጊነት፦
ስሙ ገና ሲደምቅ።
ለኢትዮጵያ ሰንደቅ፦
የሕዝብ ፍቅር አንቆት፦
እየተናነቀው!!!
እያንሰቀሰቀው!!!እምባው አልቆም ብሎት፦
የእኛ አለኝታነቱ፦
ከልቡ አቃጥሎት፦
ያደባባይ ደስታው፦ሲቃውን ፈንቅሎት፤
በጥርሱ ሳቀና፦
ተቆጣጠረና፤
ትዝ ይለኛል ያኔ?
ያውቀዋል ወገኔ?
እምባው እየፈሰሰ፤
ኃይሌም አለቀሰ።
ሁለተኛው ግና፦
ደግ አይደለምና፤
ድብን አድርጎ አይኖቹን፦ ካንጀቱ እርር ብሎ፤
ወያኔ-አጋዚን በግልፅ ተጠልሎ፤
በኒወርክ ከተማ፦
ድሉንም ተቀማ።
በእግሩ እያነከሰ፤ ብሶቱን አምጦ፤
ሕሊናውን ሰርቆ፤ ይቅርብኝን መርጦ፤
ከሕዝቡ ለመራቅ ፍፁም ባይፈልግም፤
የእንቆቅልሽ ንግዱ እድፉ-ን ባይጠርግም::
የወያኔ-አጋዚን በትግል ለመጣል፤
ሕዝቡ ደሙን ከፍሎ ነፃነት ያመጣል፤
ይሄን ልቡ ያውቃል:-
ባጣብቂኝ ከውስጡ አንገቱ ይስቃል።
እናም በሕሊናው ስለተከሰሰ፤
የመረረ እንባ፦
ኃይሌም አለቀሰ!!!

– አብይ ኢትዮጵያዊ