ደራሲ፣ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) አረፈ
“… እንደ ኪሩብ ሁሉ – ክንፍ አካል ቢኖረኝ፣መች እጠበስ ነበር – በዚህ ዓለም በቃኝ፣
ስላጣሁ ብቻ ነው – መሸሻ መድረሻ፣
በዚች በሽት ዓለም – የኖርኩ እንደውሻ …፣”
“… በሥጋዬ ብቻ ውጪ – ሀገር እስካለሁ፣
እወቁልኝ በርግጥ – አልኖርኩም ሞቻለሁ! …
ኃይሉ (ገሞራው)
Ethiopia Zare (ረቡዕ ኅዳር 3 ቀን 2007 ዓ.ም. November 12, 2014):- በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታዋቂ የነበረው ደራሲ፣ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ባለፈው እሁድ ጥቅምት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. (ኖቨምበር 9፣ 2014) በስደት በሚኖርባት ስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በ79 ዓመቱ ከዚህ ዓለም ተለየ። ሥርዓተ ቀብሩ በስዊድን እንደሚፈፀም ታወቀ።