አብሄሩም (እግዜሩም) ይቅር የሚለው ‘ቤተስኪያን’ን በሰፊው ላበላ ላጠጣ ነው

ከአ.አ.ዩ. የቋንቋ ትምህርት ክፍል መምህርና በደራሲነታቸው የሚታወቁት ዲባቶ ፈቃደ አዘዘ፣ ባንድ ወቅት ለምርምር ስራ ወደ መስክ (ገጠር) ይወጣሉ። ስራው random sampling የሚያስፈልገው እና የግድ በገበሬዎቹ ተሳታፊነት እና መሪነት መሰራት ነበረበት። ይህንኑ ለገበሬዎቹ ማስረዳትም ነበረባቸው። ለእንግሊዙ “sampling” የአማርኛው “ናሙና” አለ። “Random” የሚለውን ቃል ለማስረዳት ግን ብዙ ሲደክሙ ቆዩና “…ባልተቀናጀ መልኩ፣ ናሙና ሰዎችን እንዲሁ እየመረጡ መጠየቅ ነው…” በማለት ብዙ ቢያስረዱም ገበሬዎቹን አልገባቸውም። “ረንደምሊ… አልፎ አልፎ፣ ሰዎቹን እየመረጡ… የለ የለም። መምረጥ አይደለም። እንዲሁ እጅ እንደገባ…” ከማለታቸው፣ አንዱ ገበሬ ጣልቃ ገብቶ “አሁን ገባኝ! ‘እጅ እንደገባ ብድግ ብድግ እያደረጉ መጠየቅ ነው’ አትለንም ኖሯል?” ይላል። ፈቃደ አዘዘ “ብድግ ብድግ”ን ለንግሊዝኛው random እኩያ አማርኛ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር። … [ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ]