የማለዳ ወግ … ይድረስ ለወዳጀ ወንድም ለወዳጀ ታሪኩ ደሳለኝ!
ነቢዩ ሲራክ
ወንድሜ ሆይ ማምሻውን ”… አሁን የማወራው ስለ ብትቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሳይሆን ስለ ሆደ ባሻዋ እና ርህሩዋ እናታችን ነው!” በማለት ስለ እናትህ ጭንቀት የጻፍከውን ሳነበው፣ ስለ እናትህ ልቤ በሃዘን ተጎዳ፣ ስለ ጀግኖች ሳይሆን ስለ ጀግና እናቶች መከራ አነባሁ፣ እንደ ሰው በእልህ ሰውነቴ ጋለ፣ ተናደድኩ … በቁጭት ግን አልቆዘምኩም …!