የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መልዕክት (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ)
‹‹ለእስረኛ ማልቀስ/ ማዘን ሳይሆን የእስረኛውን መንገድ መከተል ነው››
‹‹የእስክንድር ሃሳብ ትክክል ነው›› ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከነገረን የተወሰደ
‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ በተስተናገዱ ሶስት ጽሑፎች ተከስሶ ለሁለት ዓመት ያህል የክስ ሂደቱ ሲታይ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት በከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ‹‹ጥፋተኛ›› ከተባለ በኋላ ከትናንት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዛሬ ጥዋት ላይ ከእስከዳር አለሙ፣ ይድነቃቸው ከበደ እና ስለሺ ሀጎስ ጋር ሄደን ጠይቀነው ነበር፡፡