የጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የአዙሳ ዩኒቨርሲቲ የክብር ስነ-ስርዓት መሰረዝና ያስከተለው ውዝግብ

ነሐሴ 6 2006ዓም የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛዉ ቋንቋ አገልግሎት በኢትዮጵያ መንግሥትና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን (ዳያስፖራ) መካከል ያለዉን ግንኙነት የገመገመ ዝግጅት ማቅረቡ ይታወሳል።

በዝግጅቱ ዉስጥ ከተካተቱት በርካታ ርእሶች መካከል የካሊፎርኒያው አዙሳ ፓሲፊክ ዩኒቨርሲቲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሊሰጥ አቅዶ የነበረዉ የክብር ስነስርዓት የሰረዘበት ምክንያት አንዱ ነበር። ርዕሰ ጉዳዩን አስመልክቶ የተጠናከረ ዘገባ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ መሰራጨቱን ተከትሎ፤ አንዳንድ የአሜሪካ ድምጽ ጋዜጠኞች “ሆን ብለዉ እዉነትን አዛብተዋል።” የኢትዮጵያ ሕዝብ “የዳያስፖራዉን ድምጽ እንዳይሰማ አፍነዋል” የሚሉና በተለይም አዙሳ ዩኒቬርሲቲ ሽልማቱን እንዲሰርዝ ዘመቻ ካደረጉት አንዱ ጋዜጠኛና የፖለቲካ አክቲቪስት አቶ አበበ ገላዉ ቪኦኤ ላይ…