በቻይና ከሚመረቱት ርካሽ ልብሶች ጀርባ ያለው እውነታ
በቻይናዋ ከተማ በጉዋንዡ የልብስ ስፌት ማሽን ድምጽ መስማት የተለመደ ነው። ከጠዋት እስከ ማታ ከፋሪባዎች ድምጹ በመስኮት በኩል ይሰማል።ካናቴራ፣ ሱሪ፣ ሹራብ፣ ቀሚስ ይሰፋል። ከ150 አገራት በላይ የሚላክ ምርት ነው።ፓንዩ የተባለው ሰፈር ሼን የሚባል መንደር አለ። በዓለም በፋሽን ውስጥ የሚታወቁ ልብሶች መነሻ ነው።አንድ የፋብሪካው ሠራተኛ “በወር ውስጥ ባሉት ቀናት እሠራለሁ” ትላለች።አብዛኞቹ ሠራተኞች ቢበዛ አንድ ቀን እረፍት ነው የሚያገኙት።