ኬንያ እና የዌስትጌት ጥቃት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

በኬንያ መዲና ናይሮቢ የሚገኘው ዌስትጌት የተባለው ትልቅ የገበያ ማዕከል በአሸባሪዎች ጥቃት ከተሰነዘረበት በነገው ዕለት ልክ አንድ ዓመት ይሞላል። ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደው የሶማልያ አክራሪ ታጣቂ ኃይል ታጣቂዎቹ እአአ መስከረም 21፣ 2013 ዓም ማዕከሉን በማጥቃት ለቀጠሉት አራት ቀናት በመያዝ ሕዝቡን ማሸበራቸው የሚታወስ ነው።