ሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ 250 ስደተኞች ሰጠሙ
ሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ እንደገና በሚያሰቅቅ ሁኔታ 250 ያህል ስደተኞች ሳይሰጥሙ እንዳልቀሩ ተነገረ። ከሊቢያ ባህር ኃይል በኩል እንደተገለጠው ከሆነ 250 ያህል አፍሪቃውያን ስደተኞችን ያሣፈረ ጀልባ ሰጥሟል። እስካሁን የ26 ሰዎችን ሕይወት ማትረፍ ተችሏል። የባህር ኃይሉ ቃልአቀባይ እንዳለው፣ የብዙ ሰዎች አስከሬን ባህር ላይ ሲንሳፈፍ ታይቷል።