በአደባባይ በግፍ የተገደሉት ወገኖቻችንን ዝክረ ፀሎት

በፈረንጆች አቆጣጠር በ2005ዓ.ም በኢትዮጵያ በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ “የህዝብ ድምፅ ይከበር” ብለው ሲጮኹ በአደባባይ በግፍ የተገደሉትን ከ193 በላይ ንፁኃን ዜጎችና እንዲሁም በሽዎች የሚቆጠሩ ለጋ ወጣቶችከያሉበት እየታፈሱ ወደ ደዴሳ፣ ብር ሸለቆና ሌሎች በረሃዎች ተወስደው ሳይመለሱ የጥይትና የአራዊት ራት ሆነውመቅረታቸው ይታወሳል። እነዚ ወገኖች አስታዋሽ አጥተው ደመ-ከልብ ሆነው እንዳይቀሩ በማለት በተለያዩቦታዎች የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በጋራ በመተባበር ለኖቨምበር 7/2010ዓ.ም ዕለተ ሰንበት በዓለም

አቀፍ ደረጃ በተለይም በዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮፓሊታን ብዙ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው የሚያክብሩበትናየሚዘክሩበት ትልቅ የሰማእታት መታሰቢያ ቀን በከፍተኛ ደረጃ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።

ስለሆነም የህዝባችን አጋር የሆናችሁ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በቪርጂኒያና በሜሪላንድ ግዛቶችና ከተሞች የምትገኙ ቤተክርስቲያናት፣ መስጊዶችና ሌሎች የእምነት ተቋማት በሙሉ የሕብረተ ሰቡን ደስታ ደስታችሁ፣ ሐዘኑንምሐዘናችሁ መሆኑን ከልብ ስለምናምን በግፍ ያለቁት ንፁኃን ወገኖቻችንን ለማስታወስ ከላይ በተጠቀሰው መታሰቢያ ዕለት መሰረት እንደየእምነታችሁና እንደየአካባቢያችሁ በያላችሁበት ዝክረ ፀሎት ታደርጉላቸው ዘንድ የጥቃቱ ሰለባ በሆኑት ህፃናትና እንዲሁም የሐዘን ማቅ ለብሰው ፍትሕ በተነፈጉ ወላጆቻቸው ስም ወገናዊ

ጥሪያችንን ስናቀርብ ከታላቅ አክብሮት ጋር ነው። ለምታደርጉት ኢትዮጵያዊነትና ሰብኣዊነት የተላበሰ ትብብራችሁም በቅድሚያ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

የሰማእታት መታሰቢያ ክብረ በዓል አዘጋጅ ዓለም አቀፍ ግብረ ሃይል

የበለጠ ለመረዳት (301) 326 7469, (703) 892 6166