አቡጊዳ – ግንቦት ሰባት ሻእቢያን ትቶ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር ግንኙነቱን እንዲያጠናክር ተጠየቀ
የግንቦት ሰባት አመራር የሆኑት፣ አቶ ነአምን ዘለቀ ፣ በአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ዙሪያ፣ በኢትዮጵያ ሪቪው የቀረበውን ልዩ ዘገባ «የፈጠራ ወሬ» ብለው ማጣጣላቸዉን ተከትሎ ፣ የኢትዮጵያ ሪቪው ዋና ኤዲተር የሆኑት አቶ ኤሊያስ ክፍሌ ምላሽ ሰጥተዋል።
አቶ ኤሊያስ ለኢትዮሜዲያ በሰጡት ምላሽ፣ የመን አቶ አቶ አንዳርጋቸውን ስትጠልፍ፣ የኤርትራ መንግስት እንኳን አንድ ነገር ሊናገር፣ ጭራሹን በወሩ አዲስ አምባሳደር መሾሙን በማስረዳት፣ ኤርትራ ምንም አይነት እርምጃ በየመን ላይ አለመዉሰዷን ገልጸዋል።
ትሕዴን ብዙ ሰራዊት ሲኖረው፣ አቶ አንዳርጋቸው ከአምስት አመታት በላይ ከፍተኛ ጥረት አድርገውም፣ ግንቦት ሰባት እጀግ በጣም ጥቂት ወታደሮች ብቻ እንዳሉት በማስረዳት፣ ሻእቢያ ግንቦት ሰባት ጠንካራ ኃይል ሆኖ እንዲወጣ ፍላጎት እንደሌለው አመላካች እንደሆነ አቶ ኤሊያስ ይገልጻሉ።
የየመን ጉዳይ፣ የግንቦት ሰባት ጦር ትንሽ መሆኑም፣ «የፈጠራ ወሬ ሳይሆን ማንም የሚያውቀው ፣ በአደባባይ የወጣ ሐቅ ነው» ሲሉም ለአቶ ነዓምን ምላሽ ሰጥተዋል።
ከዚህ በፊት ያጣዉን አጥቶ፣ ሌሎች ጥፋቶች ሳይከተሉና የሌሎች ብዙ ወገኖች ሕይወት አደጋ ላይ ሳይወድቅ፣ ግንቦት ሰባት ከሻእቢያ ጋር ያለውን ግንኙነት በጥሶ፣ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ደርጅቶች ጋር አብሮ መስራት እንዲጀምርም ጠይቀዋል።
«ለኢትዮጵያ ሕዝብ የማይሆን ተስፋ መስጠት አያስፈልግም» ያሉት የኢትዮጵያ ሪቪው ዋና አዘጋጅ፣ ከግብጽና ከካታር ወድ ኤርትራ ስለሚገባው ገንዘብ በተከታታይ በሚወጡ ጽሁፎች ሌሎች በርካታ መረጃዎችን እንደሚያቀርቡም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሪቪዉን ሙሉ መልስ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !
http://www.ethiomedia.com/aug14/4098.html