ወያኔና ይሉኝታ አይተዋወቁም
ጋዜጠኛ አንተነህ መርዕድ
ህወሃት በሻዕብያ ታዝሎ* ምኒልክ ቤተመንግስት ከገባና ኦነግንም ሆነ ሌሎቹን ጠፍጥፎ የሰራቸውን መናኛ ድርጅቶች እንኳ ሳያስቀርብ በብቻው የተያያዘው ዘረፋ፣ ሁሉን ለእኔ ብቻ ያለ ሂደቱ ያላስደነገጠው ኢትዮጵያዊ አልነበረም። ያለፉትን ስርዓቶች የተሻገሩ ሁለት አንጋፋ ጓደኛም ጋዜጠኞች ሲጨዋወቱ በቦታው ነበርሁ። አንደኛው ወያኔ ነፃ አወጣዋለሁ ከሚለው ከኩሩው ኢትዮጵያዊ ከትግራይ ህዝብ አብራክ የተገኘ ነበርና “ወንድሜ ይሉኝታ በትግርኛ ምንድን ነው የሚባለው?” ሲል ጠየቀው። “ይሉኝታ..ይሉኝታ…” እያለ ቃሉን ማፈላለግ ሲጀምርና ፈጥኖም ቃሉን ማግኘት ሲሳነው “ተወው ወንድሜ የሌለውን ነው የጠየቅሁህ ቃሉ ከሌለ ወያኔዎች ከየት ይማሩታል ብዬ ልጠብቅ” በማለት ሁላችንንም አሳቀን።