የያራ ሽልማት ያገኙት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ፤

ኢትዮጵያዊዉ የአፈር ሳይንስ ባለሙያና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ የኖርዌይን ዓለም ዓቀፍ ሽልማት ተቀበሉ። ሽልማት ሰጪዉ ተቋም በድረገፁ ላይ ባሰፈረዉ መረጃ መሠረት ተሸላሚዉ ፕሮፌሰር ተካልኝ የተማሩትን ትምህርት ከአካዳሚ ሚናዉ ባለፈ ለኅብረተሰብ ትልቅ ጥቅም ለሚያስገኝ ዉጤት ማዋሉ ተሳክቶላቸዋል።