የአሜሪካ እሴቶች በአፍሪካ ውስጥ ምን ፋይዳ አላቸው?
ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)
“እኛ ትክክለኛ እና ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ነገሮችን አከናውነናል፣ ሆኖም ግን ከዚህ በተለዬ መልኩም ህዝብን አሰቃይተናል፣ ከእሴቶቻችን ጋር ተጻጻሪ የሆኑ ነገሮችን ፈጽመናል። ከፍ ወዳሉ የምርመራ ስልቶች ስንገባ ማለትም ማሰቃየትን ጨምሮ ማንም ሚዛናዊ የሆነ አስተሳሰብ ያለው ሰው እንደሚያስበው እና እንደሚያምነው የምናደርገው ድርጊት ማሰቃየት ሆኖ ሲገኝ መስመሩን አለፍን ማለት ነው። እናም ይህ ጉዳይ ግንዛቤ ሊወሰድበት እና ተቀባይነትንም ማግኘት አለበት“ በማለት ፕሬዚዳንት ኦባማ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል።