በሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት የተጎዱ ሰዎችን የምትረዳው ትውልደ ኢትዮጵያዊት
በካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት እስካሁን 24 ሰዎች ሞተዋል። በሎስ አንጀለስ የምትኖረው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት ፈረደ በዚህ ሰደድ እሳት የተነሳ ለተጎዱ ነዋሪዎችን ድጋፍ ከሚሰጡ መካከል አንዷ ናት። በራሷ ተነሳሽነት ከሁለት ልጆቿ ጋር ድጋፍ አድርጋለች። በሰደድ እሳቱ እምብዛም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ እንዳልተጎዳ ተናግራለች።